የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የተለያዩ አዲስና ያገለገሉ እቃዎችና መለዋወጫዎች ሽያጭ ጨረታ

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት

የተለያዩ አዲስና ያገለገሉ እቃዎችና መለዋወጫዎች ሽያጭ ጨረታ

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አዳዲስ እና ያገለገሉ የተለያዩ የመኪና መለዋወጫዎች፣ የልብስ ስፌት ማሽን መለዋወጫዎች፣ የሠዓት መቆጣጠሪያ ማሽን መለዋወጫ፣የእንዱስትሪ ማሽኖች መለዋወጫ፣ የላዉንደሪ ማሽን መለዋወጫዎች፣ ያገለገሉ የህንፃ መሳሪያ መገልገያዎች፣ የፅዳት መገልገያ ዕቃዎች፣ ካሜራና የካሜራ አክሰሰሪዎች፣ ያገለገሉ ፕሪንተሮች፣ የኮምፕሬሰር መለዋወጫዎች፣ የእርድ ማሽን መለዋወጫዎች፣ ያገለገሉ የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎች እና ወደ ፊት በጨረታ ሰነድ ላይ የሚገለፁ ሌሎች እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ማንኛውም ተጫራች

  ያገለገሉ እቃዎችን ያሉበትን ሁኔታ በድርጅቱ በመገኘት ዘወትር በሥራ ሠዓት እስከ ጨረታ መዝጊያ ሠዓት ድረስ ማየት ይችላል፡፡

  የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀዉ መሠረት ይሆናል፡፡

  የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00/ ሀምሳ ብር/ በመክፈል ከድርጅቱ ማርኬቲንግ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መውሰድ ይቻላል፡፡

  የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች መረጃዎችን የያዘ የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፡፡

  ጨረታው መጋቢት 24 ቀን 2012 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው እለት 4፡30 ተጫራቾችና  ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ 0114-16-39-68/78 ይደውሉ፡፡

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት