በድጋሚ የወጣ የተለያዩ የእንስሳት ተረፈ ምርቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት በ2013 በጀት ዓመት ከጥር 1 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ከሚያርዳቸው እንስሳት የሚገኘውን የተለያዩ ተረፈ–ምርቶች ማለትም የዳልጋ ከብት ቁርዝ የዳልጋ ከብት የሽሆና ጅማት፣ ቀንድ ፣ የሽሆና ጥፍር እና የበግና የፍየል አንጀት ፣ የግመል ቆዳ፣ እና ሌሎች ወደፊት በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፁ ተረፈ ምርቶችን ጨምሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች፡
- በመስኩ ወይም በተመሳሳይ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት ያለውና የዘመኑ ግብር የከፈለ የማይመለስ ኮፒ በማያያዝ ማቅረብ አለበት፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ የዳልጋ ከብት ተረፈ–ምርቶች ብር 50,000 / አምሳ ሺህ ብር እና ለእያንዳንዱ በግና ፍየል ተረፈ–ምርቶች ብር 10,000 /አስር ሺህ/ በሲፒኦ ወይም በድርጅቱ ጥሬ ገንዘብ መሠብሠቢያ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት::
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (መቶ ብር/ በመክፈል ማርኬቲንግ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ መውስድ ይችላል።
- የዋጋ ማቅረቢያና ሌሎች መረጃዎች የያዘውን የጨረታ ሠነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ ከጨረታ መዝጊያ ሰዓት በፊት በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገባት አለበት::
- ጨረታው ታህሳስ 8 ቀን 2013 ዓ.ም በ4:30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ5፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ውስጥ ይከፈታል::
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ ማብራሪያ በ0114163968/78 ይጠይቁ
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት