የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ቁ.1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ፡
- ሎት1 –አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች እና ቀለሞች፣
- ሎት2-የፅዳት እቃዎች፣
- ሎት 3 የደንብ ልብስ፣
- ሎት 4 –የህትመት ስራዎች፣
- ሎት 5 –የመኪና ጎማና ተጓዳኝ ዕቃዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ጥገና መሳሪያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች ጨረታው ላይ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች፡
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፤ የtin ሰርተፍኬት ፤የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ ከገቢዎች መ/ቤት በጨረታ እንዲሳተፉ የተሰጠ ማስረጃ (ክሊራንስ)፤ የአቅራቢነት የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ማስረጃዎችና ሌሎች አባሪ ሰነዶች ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በዚሁ መሰረት የሚገዙ የተለያዩ –አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች እና ቀለሞች፣ የፅዳት እቃዎች ፣የደንብ ልብስ ህትመት፣ የመኪና ጎማና ተጓዳኝ ዕቃዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ የጥገና መሳሪያዎች ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 50 (ሃምሳ) ብር በመክፈል ከቅ/ፅ/ቤቱ 1ኛ ፎቅ ግዥ ቡድን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች በሙሉ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የመ/ቤቱን ፍላጎት በግልፅ ለማሳየት ሲባል የተወሰኑ ዕቃዎችን ናሙና መ/ቤቱ ሊያቀርብ ይችላል፡፡መ/ቤቱ ናሙና ለቀረበባቸው ዕቃዎች ተጫራቾች ናሙናዎችን በትክክል በማየት የመጫረቻ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ተ.እ.ታ/ቫት/ ጨምሮ ወይም ከተ.እ.ታ (ቫት) በፊት መሆኑን መግለፅ ይጠበቅባቸዋል፡፡ያልተገለፀ ከሆነ ተ.እ.ታ (ቫትን) ጨምሮ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የ4000 ብር CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤ ወይም ተጫራቾች ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆኑ በመ/ቤቱ ስም የተፃፈ የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋና ሙሉ ሰነድ የያዘ ፖስታ ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ ፖስታውን በሰም በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት የሚቻለው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ሲሆን ከሰኞ– ዓርብ ከ2፡30-11፡30 ሰዓት ቅዳሜ ከ2፡30-6፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅ/ፅ/ቤቱ 1ኛ ፎቅ ግዢና ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 105 የሚከፈት ሲሆን የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉልም፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡– ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተገለጸው መሰረት ለተጫረተበት ዕቃ ናሙና በድርጅቱ ማህተም ተረጋግጦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
አድራሻ፡–ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አጠገብ አንበሳ ጫማ /ዳር ማር/
ፊት ለፊት ኑር ሕንፃ አጠገብ ዳሸን ባንክ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ.105
ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ሲሆን
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-0115577122 /0115577093 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ቁ.1 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት