Bid Closing Date: Aug 15, 2019 04:00 PM
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2019
የአዲስ አበባ ሒልተን ኃ.የተ.የግ.ኩባንያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ መለዋወጫ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
- ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውን የዕቃዎችን ዝርዝር የያዘውን ፎርም ከአዲስ አበባ ሒልተን ኢንተርናሽናል ሂሳብ ክፍል የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይቻላል፡፡
- የዕቃዎቹ ዓይነቶች ዝርዝር፡
- ካርቦን ብረሽ
- ባዶ የዕቃ ማስቀመጫ ቱል ቦክስ
- የተለያየ ዓይነት ሂቲንግ ኢለመንት/ ትራንዚስተር/
- የተለያየ መጠን ያላቸው ኩሽኔት
- ያገለገለ የሳውና ማሞቂያ
- የተለያየ መጠን ያላቸው የስቲም ቫልቭ
- ለጨረታ የሚቀርብ ማንኛውም ተወዳዳሪ ሕጋዊ ፈቃድ ያለው ሆኖ ፈቃዱም በ2011 ዓ.ም የታደሰ መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የቀረቡትን ዝርዝር ዕቃዎች በሙሉ(ትልቅ ) ዋጋ ብቻ መጫረት ይኖርባቸዋል፡፡ አንዱን የዕቃ ዓይነት ነጥሎ መግዛት አይቻልም፡፡
- ዕቃዎቹን ከነሐሴ 6 እስከ ነሐሴ 8 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30-5፡30 ሰዓት እና ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 9፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ሰነዱን መግዛትና ማየት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች በጥቅል መግዛት የሚፈልጉበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ነሐሴ 9 እና 10 ቀን 2011 ዓ.ም በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት እና ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 10፡00 ሰዓት ብቻ ሒልተን አዲስ አበባ ፋይናንሽያል ኮንትሮለር ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዋጋ 10%(አሥር በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ/ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ)ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ሲ.ፒ.ኦ ያልቀረበበት እና የታደሰ የንግድ ፈቃድ የሌለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም (ከጨረታው ውጪ ይሆናል)፡፡
- ጨረታው ነሐሴ 13 ቀን 2011 ዓ.ምኮጠዋቱ አራት ሰዓት ተኩል (4፡30) ላይ ተጫራቾች ወይጫሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ሒልተን የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልጽሶ ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊውን ካሳወቅን ቀን ጀምሮ በ5 ቀን ውስጥ ገንዘቡን ከፍሎ ዕቃውን በሙሉ ማንሳት ይኖርቦታል፡፡
ሒልተን አዲስ አበባ