የጨረታ ማስታወቂያ
የአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ለ2013 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በተለፁት ዝርዝሮች በግልጽ ጨረታ ቁጥር AF01/2013 አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 ልዩ ልዩ የጄኔሬተሮች፣የሾፖችና የማሽነሪ መለዋወጫዎች
- ሎት 2 የፅህፈትና የፅዳት እቃዎች
- ሎት 3 የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ጎማና ባትሪ
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራች፡-
- ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የተከፈለበት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት
- የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት
- የታክስ ከፋይነት ምዝገባ የምስክር ወረቀትና ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ሰርተፍኬት ያለው/ያላት
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃና የትብብር ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል ማንኛውም ተጫራች
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ ለሚያቀርቡት ዕቃ ዋጋ
- የተሞላው ዋጋ ከ50,000.00 እስከ 500,000.00 ከሆነ የብር 5,000.00 በባንክ የተመሰከረለት ቼክ/CPO/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል ::
- የተሞላው ዋጋ ከ500,000.00 እስከ 1000,000.00 ከሆነ የብር 10,000.00 በባንክ የተመሰከረለት ቼክ/CPO/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል ።
- የተሞላው ዋጋ ከ1000,000.00 እስከ 5000,000.00 ከሆነ የብር 15,000.00 በባንክ የተመሰከረለት ቼክ/CPO/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል ::
- ስለዚህ ይህ ጨረታ ከወጣበት መስከረም 22 እስከ ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ/ም በተከታታይ ባሉት አስራ አምስት(15) የስራና የበአል ቀናቶች ውስጥ የማይመለስ ብር 100.00 መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ደብረ ዘይት በሚገኘው አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በዋና በር በመምጣት ሰነዱን መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥቅምት 7 ቀን 203 ዓ/ም ከቀኑ 6:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከሰዓት 7:30 ሰዓት ላይ ደብረ ዘይት ከተማ በሚገኘው ቁጥር 1 የአየር ኃይል መኮንኖች ክበብ ውስጥ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር — 011 4 3384 03 ወይም 011 4 33 80 40 የውስጥ መስመር 1330/1446 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ