የዕቃና የአገልግሎት ግዥ ግልጽ ጨረታ
ማስታወቂያ ቁጥር 01/2013
ኮሚሽን መ/ቤታችን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 01 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች የፕሪንተር ቀለሞችና የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ
- ሎት 02 ቋሚ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎች ግዥ
- ሎት 03 የሰራተኛች የደንብ ሙሉ ልብሶች የተሰፉ የሴትና የወንድ ሸሚዞች የሴቶች የቀሚስና የውስጥ ልብስ ወርቅ አና ካኪ ፖሊስተር 6000 ጨርቅግዥ
- ሎት 04 የጽዳት እቃዎች ግዥ
- ሎት 05 የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ጎማ ገጽ
በመሆኑም፡ –
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ።
- በጨረታው ለመካፈል የታደሰና አግባብነት ያለው የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ባወጣው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከብር 200.000 00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ዋጋ ባለው ግዢ ላይ የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ግብር ከፋይነት የተዘጉና የግብር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የንቅላላ ዋጋ ላይ 2% የጨረታ ማስከበሪያ Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሣጥን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰም ቤቱ የሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የመዝጊያውም ሆነ የመክፈቻው ዕለት የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ከመ/ቤቱ ፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 105 መውሰድ ይችላሉ::
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በመሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– አራት ኪሎ ከቱሪስት ሆቴል በስተጀርባ ዳኑ የአጥንት ክሊኒክ አጠገብ
ስልክ ቁጥር፡– 011-1-70-40-44
የአካባቢ የደንና የአየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን