Health Related Services and Materials / Pharmaceutical Products / Veterinary Equipment and Supplies

የአን/ጠራ ወረዳ እን/ሃ/ል/ተ/ጽ/ቤት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የእንስሳት መድሃኒት እና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ግዢ ፈጻሚው /ቤት በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የአን/ጠራ ወረዳ እን/////ቤት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የእንስሳት መድሃኒት እና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፡

 1. ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ፈቃድ ያላቸው የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /ቲን/ ከብር 50000/ ሃምሳ ብር/ በላይ ዋጋ ባላቸው ግዥዎች የሚሳተፉ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቲን/ የተመዘገበ የምስክር ወረቀት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችል
 2. ለመመዝገባቸው ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።
 3. የጨረታ ሰነዱን ገዝተው ሞልተው መፈረምና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።
 4. ተጫራቾች እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ ሞልተው በመፈረም እና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋናውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ 1% በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም በገ/////ቤት በመሂ 1(አንድ)1% የተያዘበትን ደረሰኝ በኦርጅናል ዋጋ ማቅረቢያ ውስጥ መያያዝ አለበት። በጠቅላላ የሰነዱን ኮፒዎች ለብቻው በሌላ ፖስታ በማሸግ የተያዘበትን ማስረጃ በጥንቃቄ በማሸግ የግዥ ፈጻሚው /ቤቱን፤ የተጫራቾችን ስምና አድራሻ እንዲሁም የግዥውን የዕቃ አይነት በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ቀን ከቀኑ 400 ድረስ /ቤቱ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
 5. ጨረታው በዚሁ እለት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 430 ተወዳዳሪዎች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት (ባይገኙም) በጽ/ቤቱ ቁጥር 12 ይከፈታል።
 6. 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
 7. በማንኛውም ግዥ ለእቃዎች ከብር 10000/አስር ሺህ እና ለአገልግሎት ከብር 3000/ ሶስት ሺህ ብር/ በላይ ለሚሆኑ ግዥዎች አቅራቢው ከሚፈጸምለት ክፍያ ላይ 2% ቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል።
 8. በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጪዎች ቢኖሩ /ቤታችን ተጠያቂ አይሆንም።
 9. አሸናፊው ተጫራች የአሸነፈበትን መድሃኒቶቹን በራሱ ትራንስፖርት አንጎለላና ጠራ ወረዳ ጫጫ እንስሳት ሃብት /ቤት ድረስ ገቢ ማድረግ አለበት።
 10. ማንኛውም የመድሃኒት አይነት የአገልግሎት ጊዜው 2 ዓመት ከዚያ በላይ መሆን አለበት።
 11. ተጫራ በጨረታው የአፈጻፀም ሂደት ቅሬታ ካላቸው በግዥ አዋጅ አንቀጽ 5657 እና 38 እንዲሁም በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 በአንቀጽ 39 መሰረት አቤቱታ ማቅረብ ይችላሉ።
 12. ማንኛውም ኮፒ የሚደረጉ ማስረጃዎች በትክክል መነበብና መታየት አለባቸው።
 13. ተጫራቾች በሞሉት ዋጋ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ማድረግና በፍሉድ መደለዝ አይፈቀድም
 14. አሽናፊው ተጫራች አሸናፊነቱን ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ 5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ውል ለመግባት ፈቃደኛ የሆነ።
 15. የውል ማስከበሪያ ከአሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው ከተዋዋሉት መድሃኒቶች አንድ እንኳ ቢጎድል ያስያዙት የውል ማስከበሪያ በግዥ መመሪያው መሰረት ተግባራዊ ይሆናል።
 16. አንድ ተጫራች ሌላው የሚያቀርበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም
 17. /ቤቱ የሚፈጸመው የግዥ መጠን እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 20% የመቀነስም የመጨመርም መብት አለው
 18.  የጨረታ ሰነዱ ከወረዳው /////ቤት የማይመለስ ብር 30 በመግዛት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በመግዛት መጫረት ይቻላል
 19. /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
 20. በሰንጠረዡ ላይ ከተቀመጠው ማብራሪያ ውጭ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይፈቀድም።
 21. /ቤቱ የሚገኘው ከአዲስ አበባ በስተ ሰሜን 110 / ርቀት በደሴ መስመር ላይ ነው።
 22. ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡– 0116320412 ደውለው ይጠይቁ።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የአን/ጠራ ወረዳ እን/////ቤት