ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/2013
በአብክመ በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን የአንጎት ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ለ2013 በጀት አመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴ/መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት
- ሎት፡-1 የውሃ ዕቃ
- ሎት፡-2 የመንገድ ዲዛይን አገልግሎት
- ሎት 3፡– ኤሌክትሮኒክስ
- ሎት 4፡የግንባታ ማቴሪያል
- ሎት 5 አሸዋ
- ሎት፡-6 የጽዳት ዕቃ
- ሎት 7፡– ፈርኒቸር የሚሰሩ
- ሎት 8፡– ቋሚ አላቂ የቢሮ ዕቃ
- ሎት 9-ዘመናዊ ቀፎ
- ሎት፡-10 የድልድይ ስራ ዲዛይን
- ሎት፡-11 የንፁህ የመጠጥ ውሃ የግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
- የግዥው መጠን ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡና መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር እስፔስፍኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ
- ጨረታው በሎት ስለሆነ ነጣጥሎ ወይም ከፋፍሎ መሙላት ከውድድር ውጭ ያደርጋል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 50/ሀምሳ ብር/ በመክፈል አንጎት ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት የግ/ን/አስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይቻላል ፡፡
- ማንኛውንም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን ዕቃ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ ትእዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ቢድ ቦንድ ወይም በጥሬ ገንዘብ በደረሰኝ በመቁረጥ ፖስታው ውስጥ አሽጎ አያይዞ/ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታ የሞላበትን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ አንዱን ዋና፣አንዱን ኮፒ /ቅጅ/ በማለት አ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከሎት 1-10 በ16ው ቀን እና ሎት 11 በ22ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ውጤቱ በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸንፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝና ዕቃዎችን ለማቅረብ አን/ወ/ሴ/መ/ቤቶች ባሉት የፑል ንብረት ክፍሎች ለማስረከብ ውለታ መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ መክፈቻ የመጨረሻ ቀን ዝግ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይሸጋገራል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ መረጃ ካስፈለገ አ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት የግዥ ንብ/አስ/ ቡድን በአካል በመገኘት ወይንም በስልክ ቁጥር 033 831 90 62 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
በአብክመ ሰ/ወሎ ዞን የአንጎት ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት የግዥና ንብ/አስተዳደር ቡድን