በድጋሚ የወጣ የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአንኮበር ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ት/ጽ/ቤት በላይ ጎረቤላ ቀበሌ በሴንሻይን የመንገድ ተቋራጭ የተበላሹ የውሃ መስመሮችን መልሶ ለማስገንባት እንዲቻል፡፡
የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት፡– በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው በውሃ ነክ ስራዎች እና ደረጃ 8 እና ከዚያ በላይ የሆኑ እንዲሁም የሙያ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያላቸው አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብረ ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN / ያላቸው፡፡
- ተጫራቾች በአንድ ሠነድ ከ200,000 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር /በላይ ለሆነ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ/ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታችውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከአንኮር ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ት/ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 30/ ሰላሳ ብር /በመክፈልና ዘወትር በስራ ሰዓት ለመግዛት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 ተከታታይ የካላንደር ቀን በመቁጠር ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
- በጥቃቅንና አነስተኛ ህ/ስ/ማህበር የተሰማሩ ማህበራት ደረጃውን የሚያሟሉ ከሆነ ያሉበትን ደረጃ ከአደራጃቸው ጥቃቅንና አነስተኛ ጽ/ቤት ያሉበትን ደረጃ የሚገልፅ መረጃ ማቅረብ ከቻሉ በልዩ አስተያየትም ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች ቀደም ሲል በወጡ ጨረታዎች የገባውን ግዴታ ሳያከብር በመቅረቱ ስልጣን ባለው ኣካል የታገደ ወይም ጨረታውን ባወጣው መሴት ቀደም ሲል በውሉ መሰረት ጀምረው ያቋረጡ ከሆነ በጨረታው ላይ አይሳተፉም፡፡ እንዲሁም ጨረታውን ባለማከናወናቸው በድርድር ላይ ያሉ ተጫራቾች አይሳተፉም፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በድ ቦንድ ከ1% የማያንስ በጥሬ ገንዘብ ወይም በመ/ቤቱ ህጋዊ ደረሰኝ ወይም በባንከ በተረጋጋጠ ቼክ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር ታሽጎ በማቅረብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ ሲፒኦ የሚቀርብ ከሆነ የአንኮበር ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ት ጽ/ ቤት ተብሎ ካልመጣ ቢድ ቦንድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- የጨረታ ሰነድ የሚገባው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ21 ተከታታይ የካላንደር ቀናት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጥንቃቄ በመሙላት ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻው በጥሩ ሁኔታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የሚወዳደሩበትን ሳይት በመግለፅ ኣንኮበር ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ለዚሁ ስሪ በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማሰገባት አለባቸው::
- የጨረታው የመጨረሻ የማስገቢያ ቀን በ21ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ነው፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በዚያው ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ወዳ የውኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ወይም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን የስራ ቀናት ላይ ካልዋለ በቀጣይ የስራ ቀናት በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነት ከተገለፀላቸው በኋላ በ5 ቀናት ውስጥ ቀርበው ውለታ ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ግቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊው ከተገለፀ በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋው 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ቀሪ ዝርዝር ሥራዎችን የጨረታ ሰነድ በግልፅ ዕለተዘጋጀ ከሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት ይቻላል።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በተጨማሪ ማብራሪያ፡– በስልከ ቁጥር 011 623 01 77/011 623 01 37 ደውለው ይጠይቁ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአንኮበር ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ት/ጽ/ቤት