የጨረታ መክፈቻ ቀን ስለማራዘም
አንበሳ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት በጨረታ ቁጥር አከአአድ/006/2013 ተንቀሳቃሽ የሆነ የነዳጅ መቅጃ ያለው ታንከርና ለዚሁ አገልግሎት የሚውል ናፍጣና ቤንዚን እንዲሁም ዘይትና ቅባት ለመግዛት ግልጽ ጨረታ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም ይህ ጨረታ ሐምሌ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ይከፈት የነበረው የመክፈቻ ቀኑን ማራዘም በማስፈለጉ እስከ ነሐሴ 7 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ ሲሆን፤ ማንኛውም ተጫራች እስከ ነሐሴ 7 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችሉ ሲሆን፤ ተጫራቾች ከተጠቀሰው ቀን በፊት የጨረታ ሰነዳቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እንዲያስገቡ እየገለጽን የጨረታ ሳጥኑ ነሐሴ 7 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በዋናው መስሪያ ቤት መገናኛ 24 አካባቢ በሚገኘው ኮከብ ሕንፃ 3ኛ ፎቅ የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ስልክ ቁጥር፡– 0965001465 ወይም 0965002165
አዲስ አበባ
አንበሳ የከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት