Building and Finishing Materials / Building Construction / Construction Machinery / Construction Machinery and Equipment / Finishig Works / Machinery and Equipment / Vehicle

የአነደድ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ሲሚነቶ፣ አሸዋ፣ የተለያዩ የመንገድ ስራ አገልግሎት የሚውሉ ማሽነሪዎች ፣ ኤክስካቫተር ከነሎቬዱ ኪራይ ፣ ገነቷ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ የተለያዩ ግንባታዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በጠቅላላ ዋጋ /ሎት/ ለመግዛት ይፈልጋል

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ክልላዋ መንግሥት በምስራቅ ጐጃም መስተዳድር ዞን የአነደድ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በ2013 በጀት አመት በሴክተር መስሪያ ቤቶች ከተመደበላቸው የስራ ማስኬጃ በጀት ውስጥ ከዚህ በታች በተለያየ መድብ የተዘረዘሩትን የዕቃዎች ግዥ እና ግንባታዎችን ስለሚፈጸም እንድትሳተፉ እያሳሰብን፡-

 • ሎት 1 ሲሚነቶ፣
 • ሎት 2 አሸዋ፣
 • ሎት 3 የተለያዩ የመንገድ ስራ አገልግሎት የሚውሉ ማሽነሪዎች፣
 • ሎት 4 ኤክስካቫተር ከነሎቬዱ ኪራይ፣
 • ሎት 5 ገነቷ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ፣
 • ሎት 6 የላም ጭቃ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ፣
 • ሎት 7 ጥቁር አድብር 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ግንባታ፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በጠቅላላ ዋጋ /ሎት/ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ ሲሆን፡-

 1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥረ /ቲን/ ያላቸው፣
 2. የግዥው መጠን ከብር 200 ሺህ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
 3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማሰረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
 4. የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፣
 5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 50 በመክፈል ከአነደድ ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይቻላል፣
 6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የዕቃው ዋጋ ለሎት 1- ብር 600፣ ለሎት 2- ብር 4000፤ ለሎት 3 – ብር 15 ሺህ ፣ ለሎት 4- ብር 2ሺህ 500 ፤ ለሎት 5- ብር 16 ሺህ ብር ፣ ሎት 6- ብር 16 ሺህ ፣ ለሎት 7- ብር 16 ሺህ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በመ/ቤታችን የገቢ ደረሰኝ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስተና ማስያዝ አለባቸው፣
 7. የጨረታ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 40 ቀናት ብቻ ይሆናል፡፡
 8. ተጫራቾች የጨረታ ሀሣባቸውን በአንድ ኮፒ በጥንቃቄ በፖስታ አሽገው የድርጅቱን ህጋዊ ማህተምና ፊርማውን በማድረግ ማስታዋቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ በጨረታ ሳጥኑ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በእለቱ 3፡30 ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ላይ በአነደድ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 የሚከፈት ሆኖ 16ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመማሣይ ቦታና ሰአት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሎት 5 ፤ ሎት 6 እና ሎት 7 ደግሞ በተመሣሣይ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ በጨረታ ሳጥኑ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በእለቱ 3፡30 ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ላይ በአነደድ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 የሚከፈት ሆኖ 22ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ቦታ እና ሰአት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው የሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙ ጨረታቸው ከመከፈት የማያስተጓጐል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታው ሂደት ያልተገኙ ተጫራቾች ግን በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
 9. በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚያዝበት ወቅት ያሸነፈበት ዕቃ /ንብረት/ ጠቅላላ ወጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕሻዘዝ /ሲፒኦ/ ወይም በመ/ቤታችን የገቢ ደረሰኝ ወይም በቴክኒክና ሙያ የተደራጀ ከሆነ ካደራጀው ተቋም የዋስተና ደብዳቤ ማፃፍ አለበት፡፡
 10.  አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርበው የውል ማስከበሪያ ዋስተና ፀንቶ መቆያ ጊዜ ውሉ ከሚጠናቀቅበት የመጨረሻ ቀን ጀምሮ ቢያንስ በተጨማሪ 30 ቀን ፀንቶ መቆየት የሚችል መሆን አለበት፡፡
 11. በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ያሸነፈበት ዕቃ /ንብረት/ ጠቅላላ ወጭውን በመሸፈን አነደድ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ንብረት ክፈል ድረስ ማቅረብ አለበት ሎት 1ን በተመለከተ ደግሞ በጨረታ ሰነዱ በተዘረዘረው ቀበሌዎች ማድረስ አለበት፡፡ የማሽን ኪራዮችን በተመለከተ ደግሞ በሚሰሩበት ቦታ ድረስ በራሳቸው ማጓጓዥ በማምጣት መስራት አለባቸው፤
 12. ውድድሩ በጠቅላላ ዋጋ /ሎት/ ነው፣
 13. መ/ቤቱ የተሻለ አማሪጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙለ ዩመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
 14. በግንባታ ዘርፍ ለሚሳተፉ ተጫራቾች የህንፃ ስራ ተቋራጭ በደረጃ ጂሲ/ቢሲ/9 እና ከዚያ በላይ የሆነ የግንባታ የምስክር ወረቀት ከመሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይም ከክልል ስራና ከተማ ልማት ቢሮ ማቅረብ የሚችል፤ ተቋራጮች ለግንባታ ስራ የሚያስፈልገውን የሰው ሀይል ማቴሪያልና ማሽነሪዎች ሙሉ በሙሉ እራሱን ችሎ መስራት የሚችል፡፡ በግንባታው ላይ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት 10 በመቶ የሚያወጣ ስራ ከጠቅላላ ዋጋው ላይ ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ የሚሰጥ መሆን አለበት፡፡
 15. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአነደድ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 03 በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 0582610025/26/71 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

የአነደድ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት