ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአብክመ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ
- ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ
- ሎት 2 የአላቂ የጽህፈት መሣሪያዋች ግዥ
- ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች
- ሎት 4 የህንፃ መሣሪያዎች
- ሎት 5 ፈርኒቸር
- ሎት 6 የተሽከርካሪ መለዋወጫ
- ሎት 7 የብስክሌት ጎማ
- ሎት 8 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና
- ሎት 9 ደንብ ልብስ/ብትን ጨርቅ/
- ሎት 10. የደንብ ልብስ/ጫማና የተዘጋጁ ልብሶች/
- ሎት 11 ማስክና ሣኒታይዘር
- ሎት 12 የመኪና ጐማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርት የሚያሟላ ሁሉ መወዳደር የሚቻል ሲሆን፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ሊሆኑ ይገባል፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው፡፡
- ግዥው ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር ወይም ለሚገዛው ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ህዳር 28 ቀን 2013 ዓ/ም በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአብክመ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ ቢሮ ቁጥር 31/አባይ ማዶ/ በመቅረብ የማይመለስ የኢትዮጵያ 10 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን ጨረታው ታህሣስ 12 ቀን 2013 ዓ/ም በ11፡30 ታሽጐ ታህሣስ 13 ቀን 2013 ዓ/ም በ3፡00 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከአሁን በፊት በመንግስት ግዥዎች ላይ ተሣትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን የሚኖርባቸው ሲሆን ይህ በማስረጃ የተደገፈ መሆን አለበት1፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 2180261, 0583211308 በስራ ቀንና ሰዓት መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአብክመ የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ኤጀንሲ