ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአብክመ አመራር አካዳሚ ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ፈርኒቸር /የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች / በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ አላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፣
- የግዥው መጠን 200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውነ የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡
- . ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአመራር አካዳሚው ግቢ ቢሮ ቁጥር 19 መግዛት ይችላሉ፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን /አገልግሎቶችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፣
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለጽ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ከህዳር 28/2013 ዓ.ም ጀምሮ በዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በአመራር አካዳሚው የገዥ እና ፋይናንስ ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ በሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 5 ሺህ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፣
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሣቡን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥነቃቄ በማሸግ በአመራር አካዳሚው ግዥ እና ፋይናንስ ዳሬክቶሬት ወይም ቁጥር 19 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰአት ከህዳር 28/2013 ዓ.ም እስከ Tahsas 13/2013 ዓ.ም በ4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ታህሳስ 13/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው /በተገኙበት በአመራር አካዳሚው አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- . የመክፈቻው ቀን የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሣሣይ ሰአት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- . አካዳሚው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለውም፣
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥ
- ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582262360 በመደወል ወይም
- በአካዳሚው ዌብ ሳይት www.AlA.edu.et ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የአብክመ አመራር አካዳሚ