ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የአብክመ አመራር አካዳሚ ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት 1 የፅዳት ዕቃዎች
- ሎት 2 የኤሌክትሪክ፣የውሃና የቢሮ መገልግያ ጥገና ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይገልፃል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፣
- የግዥው መጠን 200 መቶ ሺ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 20 በመክፈል በአመራር አካዳሚው ግቢ ቢሮ ቁጥር 19 መግዛት ይችላሉ፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፣
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለፅ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ከጥቅምት 2/2013 ዓ/ም ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በአመራር አካዳሚው የግዥ እና ፋይናንስ ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ በእያንዳንዱ ሎት በጨረታ ሰነዱ በተመለከተው የገንዘብ መጠን መሠረት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፣
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በአመራር አካዳሚው ግዥ እና ፋይናንስ ዳሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 19 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጥቅምት 2/2013 እስከ ጥቅምት 17/2013 ዓ.ም 4፡ዐዐ ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ጥቅምት 17/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በአመራር አካዳሚው አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የመክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ስዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- አመራር አካዳሚው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
- በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለዉም፣
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር ዐ58226236ዐ በመደወል ወይም በአካዳሚው ዌብ ሳይት www.ALA.edu.et ማግኘት ይችላሉ ፡፡
የአብክመ አመራር አካዳሚ