ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ደሴ ቅ/ጽ/ቤት ለሚያስገነባቸው የደሴ B+G+9 የግንባታ ፕሮጀክቶች የተለያዩ የግንባታ ግብአቶችን መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም
1. በደሴ ከተማ እቴጌ መነን ት/ቤት ፊት ለፊት ለሚገኝ B+G+9
- 1.1. ግቢውን ሣይት ወርክ ዲዛይን ስራ፣ የአጥር እና የጥበቃ ቤት እንዲሁም ተያያዥ ስራዎችን ዲዛይ አና ላይሲስ የስራ ዝርዝር እና ተያያዥ ጥናቶችን ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ደረጃ ስድስት/6/፣ እና ከዚያ በላይ የሆኑ አማካሪ አርክቴክቶችና መሃንዲሶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ መሣተፍ ይችላሉ፡፡
2. በደሴ ከተማ እቴጌ መነን ት/ቤት ፊት ለፊት ለሚገኘው B+G+9 ህንፃ
- 2.1. የተለያዩ ዲያሜትር ያላቸው ባህር ዛፍ አጣና/ርዝመት ስድስት ሜትርና ከዚያ በላይ የሆነ/፤ ጠጠር 00፣01፣02፣ አሸዋ፣ ብሎኬት ክላስ ቢ ባለ 20፣ OPC ሲሚንቶ፣ EGA ቆርቆሮ የተለያዩ ርዝመት ያላቸው፣ የአናፂ ሽቦ፣ የፊሮየ ሽቦ፣ G-28 ሽትሜታል፣ MJ ቦልት፣ ቦንዳ፣ የተለያየ ድያሜትር ያላቸው፡፡ ብረቶች፣ የተለያዩ PVC ኤሌክትሪክ ገመዶች፣ የተለያዩ የኤሌክትሪክ ሶኬቶችና እስዊቾች፣ የተለያዩ ድያሜትር ያላቸው U PVC፣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- 2.2. ከላይ ለተዘረዘሩት ስራዎች ለስራው ልዩ ሙያ እና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡ ማለትም፡- ፌሮየ፣ የብሎኬት መደርደር ባለሙያ፣ የልስን ስራ ባለሙያ፣ EGA ቆርቆሮ የእጅ ሙያ ስራ፣ እና የኤሌክትሪክ የእጅ ሙያ ስራ የመሣሰሉትን ማሰራት፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች ያሉት መስፈርቶችን ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች በሙሉ፡-
በዚህ መሰረት፡-
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- ለእያንዳንዱ የእጅ ሙያ ስራ ዘርፍ ስራ ለመስራት የሙያ ፈቃድ ያላቸው፣
- ተጫራቾች የእጅ ሙያ ስራ ዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለተጠየቁት ለእያንዳንዱ የእጅ ሙያ ስራ ል ምድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ቢሆ ን ይመረጣል፡፡
- የግዥው መጠን ከ50 ሺህ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ከላይ 1-4 የተጠቀሱትን መረጃዎች በሚነበብ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የዲዛይን ስራ ከላይ 1-4 የተጠቀሱትን በማሟላት ተጨማሪ በዘመኑ የታደሰ በከተማ ልማት የተሰጡ የድርጅቱ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የዲዛይን ስራ ከአሁን በፊት የሰሩበትን የብቃት ማረጋገጫ/ የመልካም ስራ አፈፃፀ/ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የዲዛይን ስራ ስራውን የሚጠይቅ የባለሙያ ስብጥር ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ላይ የሚሞሉት ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች ከአንድ ስራ ወይም ግዥ በላይ መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሞሉት የመወዳደሪያ ጠቅላላ ዋጋ መጠን 1 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ፖስታ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ በፖስታ አሽገው ስማቸውን፣ አድራሻቸውን፣ የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ዋጋ መሙየ ገጽ ላይ በማስቀመጥና ድርጅቱ ድረስ በመምጣት ለጨረታ በተዘጋጀው ማጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- 16. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ 200 ብር ብቻ በመክፈል አብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ደሴ ቅ/ጽ/ቤት ግ/ክ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 303 በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጨማሪም የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተወዳዳሪ ዋጋ ላይ ተንተርሰው መጫረት አይችሉም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ማብራሪያ ከፈለገ በስልክ ወይም በአካል በመቅረብ ማብራሪያ መጠየቅ ይችላል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅዳሜ ጨምሮ ቆይታ ይኖረዋል፡፡ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ላይ የጨረታ ሣጥኑ ታሽጐ በ4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው/የውክልና ማስረጃ ፎቶ ኮፒ በማስረከብ/ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ ህዝባዊ በአል ወይም እሁድ ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው በ4፡00 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ከተለየበት ቀን ጀምሮ ከአምስት የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የው– ማስከበሪያ ብር 10 በመቶ በመክፈል ውል ይዞ ያሸነፉበትን እቃ በታዘዘው መሠረት ጥራቱን በጠበቀ መልኩ አብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ደሴ ቅ/ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡ እቃውን የምንረከበው ጥራቱ በባለሙያ ተረጋግጦ ሲሆን ጥራቱን ያልጠበቀ እቃ የሚያቀርብ ነጋዴ እቃውን የማንቀበል መሆኑን አውቆ ለሚደርሰው ኪሣራ ድርጅቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
- አሸናፊው የሚለየው ለእያንዳንዱ የተዘረዘሩትን እቃዎች ዝቅተኛ ዋጋ የሞላ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልግ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ አብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ደ/ቅ/ጽ/ቤት ግ/ክ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 303 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 312 —ወይም 03333120114 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
- ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ያልተገለፁ ሁኔታዎች ቢኖሩ በግዥ መመሪያው ተገዥ መሆን አለባቸው፡፡
- ድርጅቱ በግዥ መመሪያው መሰረት በእያንዳንዱ እቃ ላይ 20 በመቶ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሣሰቢያ፡- 1 በዋጋ መሙያ ሰንጠረዥ ላይ ከተጠቀሰው ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ውጭ በመሰረዝ እና በመደለዝ የራሱን ስፔስፊኬሽን የሞላ እና የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም የሌለበት ሰነድ የሚያቀርብ ተወዳዳሪ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
የአብክመ ቤቶች ልማት ድርጅት ደሴ ቅ/ጽ/ቤት