ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአብክመ በምዕ/ጐጃም አስተዳደር ዞን የሰሜን ሜጫ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በወረዳው ላሉ 26ቱ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በመደበኛ በጀት ዓመታዊ ውል በመያዝ
- ሎት 1 የመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ
- ሎት 2 የሞተር ብስክሌት ጥገና የእጅ ዋጋ
- ሎት 3 ህትመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ጥገናውንና የህትመት ስራውን ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ሁሉ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው፣
- ተጫራቾች የሞሉት ጥቅል ዋጋ ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 በመክፈል ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ በሜ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በግዥ ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 38 መግዛት ይችላሉ፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ብር 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሜ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በግ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ወይም ቢሮ ቁጥር 38 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መጨረሻው የመዝጊያ ሰዓት ድረስ ማገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው መክፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ ጨረታው ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው በመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነት አይወስድም፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎት/በድምር/ ዋጋ ይሆናል፡፡
- የሞተርና የመኪና ጥገና የእጅ ዋጋ የሚወዳደሩ ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በዋጋ መሙያው ላይ ማህተምና ፊርማ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ቢሮ ቁጥር 38 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 3300432 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
የሰሜን ሜጫ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት