የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት በወረዳ ሁለት የሚገኘው የአቢሲኒያ ጤና ጣቢያ ለ2013 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን
- ሎት 1፡– መድሃኒት፤ ሪኤጀንትና የህክምና መገልገያ እቃዎች
- ሎት 2፡–ኤሌክትሮኒክስ፤ ኤሌክትሪክሲቲና ልዩ ልዩ መገልገያ መሳሪያዎች
- ሎት 3፡– አላቂ የጽህፈት ዕቃዎች
- ሎት 4 የፅዳት እቃዎች
- ሎት 5: ልዩ ልዩ የህትመት ስራዎች
- ሎት 6፡– የሰራተኛ የደንብ ልብስ እና ልዩ ልዩ የልብስ ስፌት ስራዎች
- ሎት 7፡– የህፃናት የተለያዩ የምግብ ዓይነቶች
- ሎት 8:- የጥገና ስራዎች እና ሌሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ አንዲሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት ወረዳ ሁለት አቢሲኒያ ጤና ጣቢያ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 407 በመቅረብ ሰነዱን በመውሰድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የተጫረቱበትን ዋጋ ሰነድ ውስጥ በሚገኘው የዋጋ ዝርዝር ከነቫቱ ሞልተው ያስገባሉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር በየሎቱ 5000.00 (አምስት ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ትእዛዝ (ሲፒዮ) ማስያዝ አለባቸው፡፡ ማንኛውም ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ ናሙና የማቅረቢያ ጊዜ ጨረታው ከመከፈቱ ሶስት ተከታታይ የስራ ቀናት ሲቀሩት ብቻ ነው፡፡ ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከሰዓት 8፡00 ሰዓት በጤና ጣቢያው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 0118694574/75 0118290828 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡
አድራሻ:- ድሬ ህንፃ አጠገብ ካለው ቤኒዚን ማደያ በስተጀርባ 500 ሜትር ገባ ብሎ ወይም ገሊላ ት/ቤት ገባ ብሎ ይገኛል፡፡
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት
የአቢሲኒያ ጤና ጣቢያ