የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 01/2012
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በምዕራብ ሸዋ ዞን የአቡና ግንደበረት ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ላሉት ለመንግሥት መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል
- አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎች፣
- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣
- ጀነሬተር፣
- ሞተር ሳይክሎች
- ፈርኒቸሮችና የመሳሰሉት፣
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
- የጽዳት መሣሪያዎችና
- የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል፡፡
- ከመስኩ ጋር አግባብነት ያለውና የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ሥራፍቃድ ያላቸው፣
- ተጫራቹ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ መሆን አለበት
- ተጫራቹ የግብር መለያ ቁጥር (TIN) ያለው የቫት (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ( Bid Bond )ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 14 (አሥራ አራት) ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 100 (አንድ መቶ) ከፍለው ጋዜጣው ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 14ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ከአቡና ግንደበረት ወረዳ የገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 8 በስራ ሰዓት መግዛት ይቻላል
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን የዋጋ ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ላይ ዋጋውን ከነተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) በመሙላት ስማቸውን ፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማስፈር ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶክመንታቸውን ኦርጅናልና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 በፊት ሰነዳቸውን በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሣጥኑም በዚሁ ቀን 8፡00 ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በመሥሪያ ቤቱ ቢሮ ቁጥር 8 ይከፈታል፡፡ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይሳተፉም የጨረታው መክፈቻ ይቀጥላል፡፡ የጨረታው መከፈቻ ቀን እንደአጋጣሚ የህዝብ ብሔራዊ በዓል ከሆነ የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ሰዓት እንደተጠበቀ ሆኖ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የቀረበውን የመወዳደሪያ ሀሳብ መቀየር ወይም ማሻሻል ወይም ከጨረታ መውጣት አይችልም
- አሸናፊ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የጨረታው ውጤት ከተገለጸው እስከ 10 የሥራ ቀናት ከውል ሰጪው መ/ቤት ጋር ተስማምቶ መፈረም የሚችል፡፡ ተጫራች በአካል ቀርቦ ውል ካልፈረመ ወይም ከጨረታው መውጣት ከፈለገ ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዘው(CPO)ይወረስበታል::
- ተጫራቹ በውል መሰረት የሚያቀርቡት ዕቃ ደረጃውን የጠበቀና በመሥሪያ ቤቱ ንብረት ክፍል ገቢ የሚያደርግ
- ተጫራቹናሙና ማቅረብ የሚችልና ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 26 (with holding)የሚቆርጡ
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሠረዝ ይችላል።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0919701151/0922630634/0947938525
የአቡና ግንደበረት ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት