የጨረታ ማስታወቂያ ግዥ መለያ ቁጥር 01/13
- ሎት-1 የደንብ ልብስ
- ሎት-2 አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት-3 የፅዳት ዕቃዎች
- ሎት 4 ልዩ ልዩ ዕቃዎች
- ሎት– 5 መስተንግዶ
- ሎት 6 ፈርኒቸር
- ሎት-7 ትራንስፖርት አገልግሎት
- ሎት– 8 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ሎት -9 ህትመት
- ሎት -10 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች፡
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin) የተመዘገቡበትን ሰርትፊኬት ማቅረብ አለባቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- በአቅራቢዎች ስም ዝርዝር የተመዘገቡበትን መረጃ ማቅረብ አለባቸው፣
- የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 100.00 ብር (አንድ መቶ ብር) በመግዛት በአቃ/ቃ/ክ/ከ/ወረዳ 6 ፋጽ/ቤት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ማስታወቂያዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ቆይቶ በ10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት የጨረታ ሣጥኑ ይታሸጋል፡፡ የጨረታ ሰነዱ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ የገዙትን የጨረታ ሰነድ ሙሉውን ማስገባት ይኖርባቸዋል ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) 10,000.00 /አስር ሺህ ብር በአቃ/ቃ/ክ/ከ/ወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል ስም አሠርቶ ከሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኮፒ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ ብሎ በመለየት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ናሙና ለሚያስፈልጋቸው (ከሎት 1- ሎት– 5 ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ ከ1 ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣ ከሎት 6- 10 ስለናሙናው የሚገልፅ ዝርዝር እስፔስፍኬሽን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቶች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት ሲሆን፤ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፣
- ተጫራቾች በሌሎች ተጫራቶች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት የለባቸውም፣
- የሚሞላው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፣
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– አቃ/ቃ/ክ/ከተማ ወረዳ 6 አስተዳደር ጽ/ቤት
ሣሪስ – ከሬስ ኢንጂነሪንግ ከፍ ብሎ — ስልክ ቁጥር፡– 011-8885587/ 0118-885582
አቃ/ቃ/ክ/ከተማ ወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት