Building Construction / Contract Administration and Supervision

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ኮንስትራከሽን ፅ/ቤት በከፍለ ከተማው በግንባታ ሂደት ላይ ያሉና ሊያስገነባቸው የፈለገውን ስራ አገር በቀል አማካሪዎችን አወዳድሮ በማዋዋል ለማሰራት ይፈልጋል

የአማካሪ አገልግሎት የጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር 02/2012 

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ኮንስትራከሽን ፅ/ቤት በከፍለ ከተማው በግንባታ ሂደት ላይ ያሉና ሊያስገነባቸው የፈለገውን ስራአገር በቀል አማካሪዎችን አወዳድሮ በማዋዋል ለማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የሰው ሀይል በተጨማሪም የሚቀጥሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን አንድ ብቻ መውሰድ ይችላሉ፡፡ 

 • ሎት 1 የአፄ ቴዎድሮስ ኛ ደረጃ እና የሰላምፍሬ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ጂ+0 የሆነ የመመገቢያ አዳራሽ ስራ
 • ሎት 2 የኮዬ ቁ2 ት/ቤት ጂ+0 የሆነ የመመገቢያ አዳራሽ ስራ
 • ሎት 3 ቀርሳ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ጂ+0 የሆነ የመመገቢያ አዳራሽ ስራ
 • ሎት 4 የቡልቡላ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ጂ+0 የሆነ የመመገቢያ አዳራሽ ስራ 
 1.  ደረጃቸው በኮ/ዘ/ጥ/አ/ አማካሪ ኢንተርፕራይዞች ደረጃ አንድ ለሆኑ
 2. . ለስራው ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ብቻ፣ ከኮንስትራክሽን ቢሮ የልዩ ለማማከር ስራ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው መጫረት ይችላሉ :: 
 3. ተጫራቶች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራሰአት ከላይ በተጠቀሰውቀን ውስጥ ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት የኮንስትራክሽን ምህንድስና ግዢ ቡድን ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋናው (Original) እና የማይመለስ 1 ቅጂ (copy) ይዞ በመቅረብ በነፃ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡ 
 4. ተጫራቾች የጨረታውን ሀ.ቴክኒካል ሰነድ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ (እያንዳንዳቸው በሰም የታሸጉ) ለ. ፋይናንሺያል ሰነድ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ (እያንዳንዳቸው በሰም የታሸጉ) በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እንዲሁም ሁሉንም ሰነዶች በአንድ እናት ፖስታ በሰም በማሸግ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ 7ኛ ፎቅ አዳራሽ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በአስራ ሰባተኛው የስራ ቀን የጨረታ መመሪያው በሚያዘው መሰረት የጨረታ ሰነዱን (Technical and Financial) ) ሁሉንም ሰነዶች በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ኦርጅናሉ ላይ ኦርጅናል፣ ኮፒዎቹ ላይ ኮፒ በማለት መጻፍ ያለባቸው ሲሆን፣ ይህን አለማድረግ ከውድድሩ ያሰርዛል፡፡ 
 5. ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ 7ኛ ፎቅ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የቴክኒካል ጨረታ ሰነድ ይከፈታል፡፡ 
 6.  ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከተደራጁበት ክፍለ ከተማ ወይም ህጋዊነት ካለው ተቋም የዋስትና ደብዳቤ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡
 7. የጨረታውን መመሪያ አለማክበር እና ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች አለማሟላት ከተወዳዳሪነት ያdiል፡፡ 
 8. ከአንድ ሰነድ በላይ መወዳደር፣ ከተወዳደሩበት ሁሉ ላይ ያሰርዛል፤ በተጨማሪም ተጫራቾች ሞልተው ያስገቡት ሰነድ በሁሉም ገፆች ላይ ማህተም እና ፊርማ አለማድረግ፣ የስራ ዝርዝር ዋጋ (Rate) ላይ የማይነበብ እና ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ ካለ፣ ዋጋ (Rate) ያልተሞላበት የስራ ዝርዝር እንዲሁም የስራ ዝርዝር ዋጋ (Rate) ላይ ፍሉድ መጠቀም ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡ 
 9. ማንኛውም ተጫራች የወሰደውን ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ለየብቻው በማሸግ፣ ኦርጅናሉ ላይ ኦርጅናል፣ ኮፒዎቹ ላይ ኮፒ በማለት መጻፍ ያለባቸው ሲሆን፣ ይህን አለማድረግ ከውድድር ያሰርዛል፡፡ 
 10. የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ መረዳት ይቻላል:: 
 11. አድራሻ ፡- ከቃሊቲ መናኸሪያ ፊት ለፊት በሚገኘው አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ህንጻ ላይ ሁለተኛ ፎቅ የመንግስት ኮንስትራከክሽን ጽ/ቤት የምህንድስና ግዢ ቡድን፡፡ 
 12. ልዩ አማካሪው ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ቢያንስ የሰራተኛውን 40% በክፍለ ከተማው የተመዘገበ ስራ አጥ ባለሙያ ወይም መሃንዲስ መቅጠር አለበት፡፡ ለዚህም መተማመኛ በድርጅቱ ሃላፊ ወይም ስራ አስኪያጅ የተፈረመና ማህተም ያለው ደብዳቤ የሚያቀርብ ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ አለበት፡፡ 
 13. አማካሪው ድርጅት የግንባታ ክትትል እና ቁጥጥር ስራ ይሰራል።
 14. አማካሪ ድርጅቱ ሥራውን በጥራት ለማከናወን የሚከተላቸውን መሰረታዊ ስትራቴጂዎች የሚያቀርብና እነዚህም ባለመፈጸማቸው ተጠያቂ እንደሚያደርገው ማረጋገጫ የጻፈና በስራ አስኪያጅ ወይም በሃላፊው የተፈረመና ማህተም ያለው ሰነድ የሚያቀርብ፡፡ 
 15. ልዩ አማካሪው በደረጃው እንዲያሟላ የሚጠበቅበትን የሰው ሃይል ያለውና በህጋዊ መንገድ በክፍለ ከተማችን የተመዘገቡ ባለሙያዎችን የሚቀጥር መሆኑን የሚገልጽ ሰነድ እንዲሁም ፕሮጀክቱን በጥራት ለማከናወን በቴክኒክ ሰነዱ ላይ አስፈላጊ ናቸው የተባሉ ባለሙያዎችን በወቅቱ እንደሚያሟላ በድርጅቱ ሃላፊ ወይም ስራ አስኪያጅ የተፈረመና ማህተም ያለው ደብዳቤ የሚያቀርብ
 16. . መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው 

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍስ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት የምህንድስና ግዢ ቡድን