የሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ
ማስታወቂያ ቁጥር 007/2013
በኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለ2013ዓ.ም የበጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ፡
- ሎት 1፡– የግንባታ ዕቃዎች አቅርቦት፣
- ሎት 2፡–የውሃ ማውጫ ሰመር ሰብል ፓምፕ (የውሃ ዲዋተሪንግ ጀነሬተር፣)
- ሎት3፡–የቴሌቭዥን ፣ የፍሪጅ ፣ የሳዎንድ ሪከርደር፣ የሞባይል ታብሌትና የፎቶ ካሜራ አቅርቦት፣
- ሎት 4፡ የሞተር ሳይክሎች አቅርቦት፣
- ሎት 5፡–የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች አቅርቦትና
- ሎት 6፡ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች አቅርቦቶችን በሀገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፡-
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ በዘርፉ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ በድህረ ገጽ የተመዘገቡ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር እና ከግብር ነጻ ስለመሆናቸው ክሊራንስና ሌሎች አስፈላጊ ዶክሜንቶችን ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ እያንዳንዱን ሎት 100/አንድ መቶ ብር ብቻ በመክፈል ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በአካል በመቅረብ እንዲሁም አዲስ አበባ ከተማ አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ (ጃንቦ ታዎር) አካባቢ በሚገኘው ጉዳይ ማስፈፀሚያ ቢሮ በአካል ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1፡-50,000.00(ሃምሳ ሺህ ብር)፣ ሎት 2፡– 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)፣ሎት3፡-50,000.00(ሃምሳ ሺህ ብር)፣ሎት4፡-50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)፣ሎት 5፡– 30,000.00 (ሠላሳ ሺህ ብር)፣ ሎት 6፡- 20,000.00(ሃያ ሺህ ብር) ከታወቀ ባንክ በተረጋገጠ ሲፒ.አ ወይም ለ90 ቀን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ዩኒቨርሲቲው ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን አንድ ቴክኒካል ኦርጅናል እና አንድ ቴክኒካል ኮፒ እንዲሁም አንድ ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና አንድ ፋይናንሻል ኮፒ በተለያየ የታሸገ ፖስታ በማድረግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ አዲስ አበባ ከተማ አዲሱ ገበያ በዩኒቨርሲቲው ጉዳይ ማስፈጸሚያ ቢሮ በማቅረብ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀን ተቆጥሮ በ16ኛው ቀን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 4፡00ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጧቱ 4፡15 ሰዓት ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ከጧቱ 4፡00 ተዘግቶ 415 ይከፈታል። የቴክኒካል ዶክሜንት የሚከፈተው አዲስ አበባ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ ማስፈጸሚያ ቢሮ ሲሆን የህጋዊ ዶክሜንቶችና ቴክኒካል ምዘናውን ያለፉ ተወዳዳሪዎች የፋይናንሻል ዶክሜንት የሚከፈተው በዩኒቨርሲቲው ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ አሶሳ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የፋይናንሻል ዶክመንት የሚጠቀሙት ዩኒቨርሲቲው ባዘጋጀው ዶክሜንት ላይ በመሆኑ ዋጋቸውን የሚሞሉት በዚሁ ሰነድ ላይ ይሆናል፡፡
- 12.አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን 10% በማስያዝ አሸናፊነታቸው በተገለጸላቸው በ7 ቀናት ውስጥ ውል ባይገቡ ለጨረታ ማስከበሪያነት ያስያዙት ለመንግስት ገቢ ሆኖ ዩኒቨርሲቲው የራሱን አማራጭ ይወስዳል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ ሥነ–ሥርዓት ባይገኘ የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
- ዩኒቨርሲቲው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን የዕቃዎች ሞዴል፣ ዕቃውን መቼ እንደሚያቀርብ እና የየት ሀገር ምርት መሆናቸውን በቴክኒካልና በፋይናንሻል ዶክሜንት ላይ የመግለጽ ግዴታ አለባቸው::
- አንድ ተጫራች ሌሎች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
- የቴክኒካልና የፋይናሻል ውጤት በውስጥ ማስታወቂያ ይገለጻል፣
- የርክክብ ቦታ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ይሆናል፡፡
ስለ ጨረታው የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር፡– 057 77 51 909/0769
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ
አሶሳ