የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 1/2013
ቁጥር ግፋንአስ 21/0.26/2013
በአማራ ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የአሳግርት/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ ቤት በመደበኛ በጀት
- ሎት 1 የጽህፈት መሣሪዎች ፣
- ሎት 2 ጽዳት ዕቃዎች
- ሎት 3 ደንብ ልብስ ጨርቅ ፣
- ሎት 4 ደንብ ልብስ ጫማ ፣
- ሎት 5 የተዘጋጁ ልብሶች ፣
- ሎት6 የእንሰሳት መድሀኒት ፣
- ሎት 7 የመኪናና ሞተር ጎማዎች ፣
- ሎት 8 የመኪና መለዋወጫዎች ዕቃዎች ፣
- ሎት 9 የኮንስትራክሽን ማቴሪያሎች
- ሎት 10. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣
- ሎት 11 የመኪና ኪራይ፣
- ሎት 12. ደንብ ልብስ ስፌት
- ሎት፣ 13. የመንገድ ግንባታ ማሽኖች፣
- ሎት 14 ዘይትና ቅባት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታ ሰመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች ያለውን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው።
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00/ ሁለት መቶ ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አጠቃላይ የተወዳደሩበትን ዋጋ ቫቱን ጨምሮ 2 % በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ በደብዳቤ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
- አሸናፊው ድርጅት ጽ/ቤቱ አሸናፊነቱን ከገለፀለት ቀን ጀምሮ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በውሉ መሰረት ዕቃውን ማቅረብ አለባቸው።
- በተጫራቾች የተሞላ የጨረታ ሠነድ መ/ቤቱ ሰነዱን እንዲሸጥ ባስቀመጠው ከ3/02/2013 ዓ.ም ጀምሮ 16 ቀን ተከታታይ ቀናት በመ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማንኛውም የስራ ሰአት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ/ በሰም ባይታሸግም/ዋናና ቅጂ በማለት ሙሉ አድራሻ በመፃፍ የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀን በ16ኛው ቀን ማለትም በ18/02/2013 ዓ.ም የጨረታው ሣጥን ከጠዋቱ 3፡30 ሠዓት ይታሸጋል በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
- የጨረታው መከፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ከዋለ በተከታዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሎት የተገለፀውን ሰነድ ከአሳግርት ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በመሄድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ሰመከፈል መግዛት ይችላል።
- አሸናፊው ድርጅት የአሸነፈውን ዕቃ ንብረት አሣ/ወ/ገ/ት/ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለበት።
- መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲያንስ ለ2 ወር የጊዜ ገደብ ያለው መሆን ይኖርበታል።
ማሳሰቢያ፡– አሸናፊው ድርጅት ጥራት ያለው ዕቃ በወቅቱ አስገብቶና ሂሳቡን በወቅቱ የሚጸደቅ መሆን አለበት ።
- ወድድሩ በሎት ስለሆነ ማንኛውም ተወዳዳሪዎች በሎት ውስጥ የተዘረዘሩት ሁሉ ዕቃዎች ዋጋ መሙላት ይጠበቅባቸዋል ።
- ሳምፕል (ናሙና ) የሚያስፈልጋቸውን እቃዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት ፅ/ቤቱ ያቀረበ ስለሆነ ሰነዱን በሚገዙበት ሰአት በማየት ወይም በፎቶ በማንሳት በጥንቃቄዋጋ መሙላትይጠበቅባችኋል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-0116240394 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
ወረዳው የሚገኝበት ርቀት ከአዲስ አበባ በ25 ኪሜ አና ከደ/ብርሃን በ74ኪሜ ላይ ይገኛል።
በአብክመ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ
የሰሜን ሸዋ ዞን አሳግርት ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት