የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2013 ዓ.ም
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት በ2013 በመደበኛ በጀት የመኪና ጎማ እና የደንብ ልብስ ግዥ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ካላቸው ነጋዴዎች ላይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች፡
- በሚወዳደሩበት ዘርፍ የዘመኑ ግብር የከፈሉና የተሟላ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የTIN No ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የንግድ ምዝገባ ቁጥርና የተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ግብይቱ ከ200000 ሺ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተጨማሪ እሴት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሀሳብ መስጫ ስማቸውን ፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ሆኖ ለወደፊት በመንግስት የሚወጣ ጨረታ እንዳይሳተፉ ሊደረግ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ 100 ብር በመክፈል የክፍያና ሂሳብ ደጋፊ የስራ ሂደት ማግኘት ይችላሉ
- የሚገዙትን ማቴሪያሎች ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) ከሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋናውና ኮፒውን ብቻ ለብቻ ሁሉም የንግድ ማስረጃዎቻቸው ጋር በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ከ29/01/2013 እስከ 13/02/2013 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ ለ15 ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን 16ኛው ቀን ማለትም 14/02/2013 በ4፡00 ሰዓት የሚታሸግ ይሆናል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን በ14/02/2013 ዓም ከጠዋቱ በ4፡30 በአ/ፉ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ቢሮቁጥር 01 በግልፅ የሚከፈት ሲሆን ምናልባት 16ኛው ቀን የህዝብ በዓል ወይም ከመንግስት የስራ ቀን ውጭ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 1% በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ጋራንት (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ሰዓትካለፈ በኋላ የመጣ የጨረታ ሠነድ ከጨረታ ሳጥን ውስጥ ሳይገባ ተመላሽ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታው ለመስሪያ ቤቱ አዋጭ በሆነው መንገድ ማለትም በሎት ወይም በተናጥል ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 0334490340/ 0334490061/ ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አድራሻችን፡–ጨፋ_ሮቢት ከተማ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ መስመር 300 ኪ/ሜ ላይ እንገኛለን፡፡
በአብክመ የአሮሞ ብ/ዞን አ/ፉ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት