የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር ግ/ጨ/13/2013 ዓ.ም
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለመረጃና መገናኛ ቴ/ዳ/ጽ/ቤት ለሥራ አገ/ት የሚውሉ የተለያዩ የአይሲቲ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
- Lot 1 – Supply, installation, configuration implementation, Traning and commissioning of unified threat management solution (UTM) and Multilayer core switch,
- Lot 2- Supply, installation, configuration implementation, training, and commissioning of digital signage solutions.
- Lot 3 Supply, installation, configuration implementation, training and commissioning of 200 KVA silent Diesel Generator and supply of IKVA single phase online double conversion UPS.
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የንግድ ድርጅቶች፡-
- በዘርፉ ህጋዊ እና የታደሰ ኦርጅናል የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ሊስት (ዝርዝር) የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የተጨማሪ እሴት ታከስ /VAT/ የምስክር ወረቀትና የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ኦርጅናልና የድጋፍ ደብዳቤ ከገቢዎች ባለስልጣን ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ካደራጃቸው አካል የሚሰጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የተመዘገቡበትን /PPA Online/ የምዝገባ ሰርተፊኬት ከሲፒኦ ጋር አብሮ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ስለ ጨረታው የሚገልጸውን የጨረታ ሰነድ ከኣርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከግዥ አገ/ት ቡድን በአዲሱ አስተዳደር ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 112 ወይም አዲስ አበባ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ጉዳይ ማስፈፀሚያ ጽ/ቤት አራት ኪሎ ሮሚና ካፌ ቢሮ ቁጥር 14 ዘወትር በሥራ ሰዓት ለፋይናንስና በጀት አስ/ር/ዳ/ጽ/ቤት ለምድቡ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተቋቋሙበትን የሕጋዊነት ማስረጃ በማሳየት ያለ ከፍያ በነፃ ይሰጣቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኤንቬሎፕ በ17/5/2013 ዓ.ም ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አገ/ትና ንብረት አስ/ር/ዳ/ጽ/ቤት ቢሮ በተዘጋጀ ሳጥን መከተት ይቻላል፡፡ ጨረታዉ የሚከፈተው በ4፡30 ላይ ይሆናል፡፡ ሰነዱ ታሽጐ ሳይቀርብና ተፈላጊ ሰነዶች ቢጐድልበት ኃላፊነቱ የተጫራቹ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/ቢድ ቦንድ/ ሎት 1. 180,000.00/አንድ መቶ ሰማንያ ሺህ ብር/ ሎት 2. 30,000,00/ሠላሳ ሺህ ብር/ ሎት 3 45,000.00/አርባ አምስት ሺህ ብር/
- በግዥ መመሪያ አንቀጽ 16.16.4 መሰረት ተገቢውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው:: የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ካደራጃቸው ኣካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው:: በጨረታው በተናጠል የሚወዳደሩ አቅራቢዎች ጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከጨረታው ሰነድ በማየት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በከፈታው ቀን ከተጠቀሰው ሰዓት ውጪ ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- የቴከኒካል ዶክሜንት እና ህጋዊነት ሰነዶችና CPO ለብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ የፋይናንሻል ዶከመንት ለብቻው ታሽጎ የቴክኒከ ውድድሩን ያለፉት ድርጅቶች ብቻ እንዲከፈት ይደረጋል።
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅቶች ከዩኒቨርሲቲው ጋር ውል በመግባት ማንኛውንም ወጪ በራሳቸው ችለው ለዩኒቨርሲቲው ንብረት ክፍል ገቢ ያደርጋሉ፡፡
- 1ተጫራቾች ማንኛውንም የመንግስት ታክስና የግብር ግዴታቸውንም ከነመጓጓዣው በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ነጠላ ዋጋ ውስጥ አካተው ማቅረብ አለባቸው::
- ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያከዚህ በታች በተጠቀሱ አድራሻዎች ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ስልክ ቁጥር +251111577704 /አዲስ አበባ/
ስልክ ቁጥር 0468811415/0468814533
/አርባ ምንጭ/
የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ