የግንባታ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የገዥ መለያ ቁጥር /ግ/ጨ/001/2013 ዓ.ም
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለ2013 በጀት ዓመት ለግርጫ ምርምር ማዕከል የወተት ላሞች ቤት ግንባታ (Construction of Barn Building Project) ሥራ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፤
- Lot 1. Construction of Barn Building Project ግንባታ ሥራ
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የንግድ ድርጅቶች፡-
- በዘርፉ ህጋዊ እና የታደሰ ኦርጅናል የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ሊስት (ዝርዝር) የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የምስክር ወረቀትና የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ኦርጅናልና የድጋፍ ደብዳቤ ከገቢዎች ባለስልጣን ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ካደራጃቸው አካል የሚሰጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በኢፌዲሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የተመዘገቡበትን /PPA Online/ የምዝገባ ሰርቲፊኬት ከሲፒኦ ጋር አብሮ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ስለ ጨረታው የሚገልፀውን የጨረታ ሰነድ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከግዥ አገ/ት ቡድን በአዲሱ አስተዳደር ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 112 ወይም አዲስ አበባ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ጉዳይ ማስፈፀሚያ ጽ/ቤት አራት ኪሎ ሮሚና ካፌ ቢሮ ቁጥር 14 ዘወትር በሥራ ሰዓት ለፋይናንስና በጀት አስ/ ር/ዳ/ጽ/ቤት ለሎት 1 እና ለሎት 2 ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር/ በመግዛት መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት የተቋቋሙበትን የሕጋዊነት ማስረጃ በማሳየት ያለ ክፍያ በነፃ ይሰጣቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኤንቬሎፕ በህዳር 28/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አገ/ትና ንብረት አስ/ር ዳ/ጽ/ቤት በተዘጋጀ ሳጥን መከተት ይቻላል ጨረታው የሚከፈተው በ4፡30 ላይ ይሆናል። ሰነዱ ታሽጎ ባይቀርብና ተፈላጊ ሰነዶች ቢጎድልበት ኃላፊነቱ የተጫራቹ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪ ሲፒኦ/ቢድ ቦንድ ሎት 1 ብር 100,000.00/አንድ መቶ ሺህ ብር/
- በግዥ መመሪያ አንቀጸ 16.16.4 መሰረት ተገቢውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው። የጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ካደራጃቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው:: በጨረታው በተናጠል የሚወዳደሩ አቅራቢዎች ጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከጨረታው ሰነድ በማየት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታው ቀን ከተጠቀሰው ሰዓት ውጭ ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- የቴክኒካል ዶክሜንት እና ህጋዊነት ሰነዶችና CPO ለብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል:: የፋይናንሻል ዶክመንት ለብቻው ታሽጎ የቴክኒክ (ውድድሩን ያለፉት ድርጅቶች ብቻ እንዲከፈት ያደረጋል።
- በጨረታው ላይ መወዳደር የሚችሉት ተጫራቾች ደረጃ – 5 እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው፤
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅቶች ከዩኒቨርሲቲው ጋር ውል በመግባት በውል ጊዜ መሠረት ግንባታ ሥራውን ሰርቶ የማቅረብ ግዴታ አለበት።
- ተጫራቾች ማንኛውንም የመንግስት ታክስና የግብር ግዴታቸውንም በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ነጠላ ዋጋ ውስጥ አካተው ማቅረብ አለባቸው።
- ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭካገኘጨረታውንበከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ከዚህ በታች በተጠቀሱ አድራሻዎች ደውሎ መጠየቅ ይቻላል::
ልክ ቁጥር +251111577704 አዲስ አበባ!
ስልክ ቁጥር 0468811415/0468814533/አርባ ምንጭ፤
የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ