የጨረታ ማስታወቂያ ቁ-01/2013
የአርሲ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በ2013 የበጀት ዓመት በዞኑ ለሚገኙ ጽ/ቤቶች አገልግሎት
- የሚውሉ ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፤
- ፈርኒቸር፣
- የጽህፈት መሣሪያዎች፣
- የጽዳት እቃዎች፤
- የሠራተኞች የደንብ ልብስ፤ እና
- የመኪና ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም:-
- ለተጠየቁት የግዢ እቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No.) ያላቸው እና በፌደራል፤ በክልል ወይም በዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ወይም በግዢዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፤ ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች፣ እና ለጽህፈት መሣሪያዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) እንዲሁም፧ ለጽዳት እቃዎች ፤ ለሠራተኞች የደንብ ልብስ እና ለመኪና ጎማዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 150.00 (አንድ መቶ ሃምሳ) በጽ/ቤቱ ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር 1000022696134 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የፋይናንስ አስተዳደር የሥራ ጉዳይ ቢሮ ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመክፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 6ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን፤ ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጽ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለኤሌክትሮኒክስ እና ለመኪና ጎማዎች ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ብር 25,000.00 (ሃያ አምስት ሺህ)፣ ለጽህፈት መሳሪያዎች ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ) ፤ ለፈርኒቸር እና ለጽዳት እቃዎች ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ብር 7,000.00 (ሰባት ሺህ) እንዲሁም፧ ለሠራተኞች የደንብ ልብስ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺህ) በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የታወቀ ባንክ በከፍያ ማዘዣ (CPO) ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- በማይክሮ ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ ማህበራት ከላይ በተራ ቁጥር 5 ላይ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ ከተገለጸው የጨረታ ሠነድ ማስከበሪያ የብር መጠን ጋር የሚመጣጠን የዋስትና ደብዳቤ ካደራጃቸው አካል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ክምችት ያለውና እቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ አሰላ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የዞኑ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር (0222381142) (0911066944) (0912311526) (091226032) ይጠይቁ፡፡
የአርሲ ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት