የጨረታ ማስታወቂያ
የአራዳ ክ/ከተማ የወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ በ2013 በጀት ዓመት የ1ኛ ዙር አገልግሎት የሚውሉ
- የፅህፈት መሳሪያዎች፤
- የፅዳት እቃዎች፣
- የደንብ ልብሶች
- ህትመቶች፣
- አላቂ የህክምና እቃዎች፤
- ቋሚ የህክምና እቃዎች እና የተለያዩ ቋሚ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ::
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ እና ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የገበረ እና የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር የአቅራቢነት ምዝገባ ያደረገ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር ሰነዱን ብር 50.00 (ሀምሳ ብር) በመከፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጀምሮ ለ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ። ጨረታው በ11ኛ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው እለት 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች ወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ ንብረት ክፍል መሉ ወጪውን ችለው ማሰረከብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስረከቢያ ብር 2% ከባንክ በተመሰከረ ቼክ በጥሬ ገንዘብ ወይም በCPO ማስያዝ አለባቸው :: ሙሉ ዝርዝር መረጃው ከሰነዱ ላይ መመልከት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ከገዙት ጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም ::
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው :
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች በሰም የታሸገ ኤንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው፡፡
አድራሻ፡– በአራዳ ክከተማ ወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ ሰሜን ሆቴል ጀርባ ሲ.ሲ.ኤፍ ግቢ አጠገብ ::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-011 126 52 92/011 111 96 29 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 5
አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ