የጨረታ ማስታወቂያ
የአራዳ ክ/ከተማ የወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የተለያዩ አገልግሎቶች ላይ የዋሉ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ከነዚህ ዕቃዎች ውስጥ
- የብረት መደርደርያ፣
- ተሽከርካሪ ወንበር ፤
- መደበኛ ወንበር ትራዞ ታይል (የተከማቹ የድንጋይ ፍርስራሾች እና ሌሎች በርካታ አገልግሎት የሰጡ ዕቃዎች ሲሆኑ ተጫራቾች ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው የሚሞላው በጥቅል ዋጋ ነው።
- አሸናፊ ተጫራች ዕቃዎችን በ5 ቀን ውስጥ ማንሳት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ሞልቶ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የዋጋ ማስከበሪያ 10 ፐርሰንት በሲፐኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
- ተጫራቾች ከመወዳደራቸው በፊት ዕቃዎችን በአካል ቀርቦው ማየት ይችላሉ ::
- ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው እለት 4፡30 ሰአት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
- አድራሻ፡– በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 5 አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ ከሰሜን ሆቴል ጀርባ ሲ.ሲ.ኤፍ ግቢ አጠገብ ::
ለበለጠ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር 011 126 52 92/ 011111 96 29 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 5
አፍንጮ በር ጤና ጣቢያ