የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 09/2012
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአራዳ ክፍለ ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በከፍለ ከተማው ሊያስገነባቸው የፈለገውን ስራ የሚሠሰራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን፣ የሰው ሀይል እና የሚቀጥሉትን መስፈርቶች በማሟላት የጨረታ ሰነዱን አንድ ብቻ መውሰድ ይችላሉ፡፡
ሎት |
የሥራው ዓይነት |
የሚሰሩበት ወረዳ
|
ደረጃ
|
የጨረታ ሰነድ መሸጥ የሚጀመርበት ቀን |
የጨረታ ማስገቢያ ቀን
|
የጨረታ መክፈቻ ቀን |
1 |
መሀል ግንፍሌ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት፣ የቀበና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት መመገቢያ እና ማብሰያ ግንባታ |
ወረዳ7
|
GC5/BC5 እና ከዚያ በላይ
|
በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የሥራ ቀን 10 ሰዓት ድረስ
|
በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ
|
በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን 4፡30 ሰዓት ጀምሮ
|
2 |
ራስ አበበ አረጋይ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት፣ ኒውኤራ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት እና ኢትዮጵያ ዕድገት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት መመገቢያ እና ማብሰያ ግንባታ
|
ወረዳ 5፡54 |
GC5/BC5 እና ከዚያ በላይ
|
በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የሥራ ቀን 10 ሰዓት ድረስ |
በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ
|
በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን 4፡30 ሰዓት ጀምሮ
|
- በዘርፉ 2012 የታደለ ህጋዊ ፈቃድያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚ/ር የስራ ተቋራጭ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው ዋናውንና የማይመለስ ኮፒ በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ከመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ዋናውንና አንድ ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ሥራ ተቋራጭ ሆነ አማካሪ ከመስተዳድሩ ኮንስትራከሽን ቢሮ ተመዝግቦ የብቃት ማረጋገጫ ወይም የአጭር ምዝገባ ሰርተፍኬት ሳይዝ በሴክተሩ መሳተፍ አይችልም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር /በመክፈል በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ህንጻ ኮንስትራከሽን ጽ/ቤት 3ተኛ ፎቅቀርበው በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና Bid Bond 70,000 ብር ከታወቀ ባንክ በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ ለ90 ቀናት የሚያገለግል ሆኖ ከኦርጅናል ቴክኒካል ጨረታ ሰነዱ ጋር ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡
- በተጨማሪነት ስራውን በምን ያህል ጊዜ እንደሚያጠናቅቁ የሚገልጽ የስራ መርሃ ግብር /ወርክ ስኬጁል/ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ፣ ፋይናንሻል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለትኮፒ በድምሩ ስድስት ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም በሰም ታሽገውን 6 ፖስታ በአንድ እናት ፖስታ የድርጅቱንና የተወዳደሩበት ስም በመጻፍ በሰም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተቋራጮች የስራዎችን የዋጋ ዝርዝር እና የጨረታ ማወዳደሪያ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን አድራሻቸውን ማስፈር ማህተም ማድረግ ኤንቨሎፑን በሰም በማሸግ ማስታወቂያው በወጣበት በ11ኛው ቀን አራዳ ክ/ከተማ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 4፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለበት መሆን አለበት ይህም ከሆነ ተጫራቾች ያስገባው ሰነድ ውድቅ ይሆናል::
- በኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በወጡና በሚወጡ የግንባታ ጨረታዎች ላይ ተቋራጭ ከአንድ በላይ ጨረታ መሳተፍ አይቻልም፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታውን ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በአራዳ ክ/ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ይከፈታል የጨረታው መከፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ የአራዳ ክ/ከ ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ምህንድስና ግዥ ቡድን በግንባር በመቅረብ መረዳት ይችላሉ፡፡
የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት