Construction Machinery / Construction Machinery and Equipment / Machinery and Equipment / Others

የአምቦ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለመንገድ ሥራ የሚያገለግል ጋረጋንት የሚያመርት ዶዘር (D8R Bulldzer CAT) የፈረስ ጉልበቱ 305 (ሶስት መቶ አምስት) የሆነ በሰዓት አወዳድሮ በኪራይ ለማሰራት ይፈልጋል

መጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2013

የአምቦ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር /ቤት ለመንገድ ሥራ የሚያገለግል ጋረጋንት የሚያመርት ዶዘር (D8R Bulldzer CAT) የፈረስ ጉልበቱ 305 (ሶስት መቶ አምስት) የሆነ በሰዓት አወዳድሮ በኪራይ ለማሰራት ይፈልጋል፤

 ስለዚህ፡

 1. ከተጠየቀው ስራ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው፤ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያለው፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ተመዝጋቢ እንዲሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር/Supplier List/ የተመዘገበ ሆኖ ከሚመለከተው አካል የማስረጃውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል  መሆን አለበት፡፡ በተጨማሪም ከሚያገኘው ገቢ ላይ 2% ታክስ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ፤
 2. ከሙስና እና መሰል ብልሹ አሠራር ድርጊቶች ነፃ የሆነ የሀገሪቱንና የክልሉን ሕግ የሚያከብር፤
 3. ከቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2% በአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ //ቤት ስም CPO የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ የሚችል፣
 4. ከአሸነፈ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋ ላይ የጨረታ ውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ የሚችል
 5. በጨረታ ሠነዱ ላይ ስልጣን ባለው አካል/የድርጅቱ ባለቤት/ ሥም ፊርማ፤ የድርጅቱን ማህተም፤የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር በፖስታ ላይ መገለፅ ይኖርበታል፡፡
 6. ተጫራቾች የጨረታውን ኦሪጅናል ከኮፒው ጋር በሰም በታሸገ ፖስታ አድርጎ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
 7. ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን፤ 18/02/2013 4:30 የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 5:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
 8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአምቦ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር /ቤት በቢሮ ቁጥር 07 ይከፈታል:: ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባለመገኘታቸው ምክንያት ጨረታውን ከመከፈት አያስቀርም:: ጨረታው የሚዘጋበትና የሚከፈትበት የአድራሻ ለውጥ ካለ በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
 9.  የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 100/ መቶ ብር/ በመክፈል በአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር /ቤት ሥም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ በባንክ ሂሳብ ቁጥር GOV 1412 ወይም 1000015202018 በማስገባት ባንኩ የሚሰጠውን ደረሰኝ/sleep/ በአምቦ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ገቢ በማድረግ ሰነዱን በአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር /ቤት ቢሮ ቁጥር 07 መውሰድ ይቻላል፡፡
 10.  አሸናፊ የሆነ ተጫራች አሸናፊ የሆነበትን በደብዳቤ ከተሰጠው ቀን ጀምሮ 7(ሰባት) ባልበለጠ ቀናት ውስጥ /ቤታችን በአካል ቀርቦ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መፈረም አለበት::
 11.  ጨረታውን ለማደናቀፍ የሚሞክር ተጫራች ከጨረታው ውጪ እንዲሆን ተደርጎ ለወደፊቱ በማንኛውም የመንግስት ግዥ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
 12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 011260-94-48/01123644-62

አድራሻ፡አምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር

አምቦ ከተማ አስተዳደር አምቦ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር /ቤት