ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2013
የአምቦ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ለአምቦ ከተማ አስተዳደር መስሪያ ቤቶች የሚያገለግሉ
- የፅህፈት መሣሪያዎች፣
- የፅዳት መሣሪያዎች፣
- ደንብ ልብስ፣
- ኤሌክትሮኒክስ፣የቤትና የቢሮ ዕቃዎች፣
- የመኪና ጎማ፣
- ለቴክኒክ ስልጠና እና ሙያ መግዛት ለሚፈልግ አስፈላጊ የሆኑ መስፈርቶችን የሚያሟሉ አቅራቢ ድርጅቶችን በማወዳደር ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል ፣
ሰለዚህ
- ከተጠየቀው ስራ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው የ2013 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin Number) ያለው፤ የዘመኑን ግብር የከፈለ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ፣ እንዲሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር /Supplier List/ የተመዘገበ ሆኖ ከሚመለከተው አካል የማስረጃውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት። በተጨማሪም ከሚያገኘው ገቢ ላይ 2% ታክስ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ
- ከሙስና እና መሰል ብልሹ አሠራር ድርጊቶች ነፃ የሆነ የአገርንና የክልሉን ሕግ የሚያከብር፤
- ከቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 2% በአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ት/ጽ/ቤት ስም CPO የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ የሚችል ፤
- ካሸነፈ በኋላ ከጠቅላላ ዋጋ ላይ የጨረታ ውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ የሚችል፣
- በጨረታ ሠነዱ ላይ ስልጣን ባለው አካል /የድርጅቱ ባለቤት ሥም፤ ፊርማ፤ የድርጅቱን ስም፤ፊርማ፣የድርጅቱን ማህተም፣ የድርጅቱን ሙሉ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር በፖስታ ላይ መግለጽ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ኦሪጅናል ኮፒው ጋር በታሸገ ፖስታ አድርጎ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን፣ በ25/01/2013 (8:30 የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ9:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአምቦ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በቢሮ ቁጥር 07 ይከፈታል። ጨረታው ከሚከፈትበት ቀን ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባለመግኘታቸው ምከንያት ጨረታውን ከመከፈት አያስቀርም። ጨረታው የሚዘጋበትና የሚከፈትበት የአድራሻ ለውጥ ካለ በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር በመክፈል በአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤትም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ በባንክ ሂሳብ ቁጥር GOV 1412 ወይም 1000015202018 በማስገባት ባንኩ የሚሰጠውን ደረሰኝ /Sleep/ በአምቦ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ግቢ በማድረግ ሰነዱን በአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 07 መውሰድ ይቻላል፡፡
- አሽናፊ የሆነ ተጫራች አሸናፊ የሆነበትን ዕቃ በደብዳቤ ከተሰጠው ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መፈረም አለበት
- ጨረታውን ለማደናቀፍ የሚሞክር ከጨረታው ውጪ እንዲሆን ተደርጎ ለወደፊቱ በማንኛውም የመንግስት ግዥ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡ – በኦሮሚያ ክልል ምዕ/ሸዋ ዞን የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡– 011 260 94 48/011236 44 62
የአምቦ ከተማ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት