የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ
ቁጥር 002/2013
የአምበርቾ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ኃላ/የተወሰነ በደቡብ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት በከምባታ ጠምባሮ ዞን ለሚገኙ አርሶ አደሮች በ2013 ዓ/ም አዳማ፣ ሻሸመኔና ሃላባ ከሚገኙ ማዕከላዊ መጋዘኖች ለሰብል አብቃይ ወረዳ ጣቢያዎች ለበልግና መሕር እርሻ የሚውል የአፈር ማዳበሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ተጫራቾች ከድርጅቱ የማራገፊያ ጣቢያዎችን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ በመውሰድ ለማጓጓዝ የሚፈለገውን ጭነት የማድረሻ ዋጋ በጠጠርና በአስፋልት መንገድ በአማካይ በኩ/ል በአንድ ኪሎ ሜትር አስልተው በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
በዚሁ መሠረት፡-
- በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር ከፍሎ የንግድ ፈቃዱን ያሳደሰ እንዲሁም የግል ትራንስፖርት ድርጅት ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፣
- ከሚመለከተው ፈቃድ ሰጪ መንግስታዊ አካል የምዝገባ ምስክር ወረቀት የሚመለስ ዋናና የማይመለስ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፣
- ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የሥራ ዘርፍ ተሰማርቶ ሥራውን በሚገባ ስለመወጣቱ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል፣
- የጨረታው ተሳታፊዎች ለአስተዳደር እንዲያመች ሲባል በአንድ ወረዳ ውስጥ በከፊል ዋጋ ማቅረብና መወዳደር አይችሉም፣
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብር 120,000/አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ አሸናፊ የሚሆን ማንኛውም ድርጅት ውል ከመፈፀሙ በፊት ያሸነፈበትን ጭነት የማጓጓዣ ዋጋ 10% በቅድሚያ ያስይዛል፡፡
- ተጫራቾች የተሽከርካሪዎች ዝርዝር ቢያንስ 2,000/ሁለት ሺህ/ ኩንታል በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚችሉ መኪናዎችን /የሰሌዳ ቁጥር፣ የመኪና ዓይነትና የመጫን አቅም/ የሚያስረዳ ፈቃድ ከሰጠው መንግስታዊ አካል የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች ግዴታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከአምበርቶ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን ኃ/የተ ዋና ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታውን ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይችላል፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒየኑ ዋና ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ነገር ግን 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሁኔታ ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡ ዱራሜ ከተማ ከከምባታ ጠምባሮ ዞን ፍርድ ቤት ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር፡-046-554-0931/0925521215/0913028144
የአምበርቾ የገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒያን
ኃላፊነቱ የተወሰነ ዱራሜ