የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር አ.ገ.መ .ኮ.ኤ 02/2013 ዓ.ም
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራከሽን ኤጀንሲ ዳይናማይትና እና ኤሌክትሪካል ዲቶኔተር ከአቅራቢ ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች መሠረት በማድረግ በጨረታው እንዲወደሩ ተጋብዘዋል፡፡
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላት
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው::
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ከልዩነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተቁ 3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ፣ የተጫራቾች መመሪያ፣ የውል ረቂቅ፣ የዋጋ መሙያ ፎርምና ቴክኒክ መግለጫ ያያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ አማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ዋናው ቢሮ ባህርዳር ከተማ ከሚገኘው ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 12 የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የጠቅላላ ዋጋውን 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከፋይናንሻል ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለባቸው፣
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በሁለት ቅጆችማለትምቴከኒካልና ፋይናንሽያል በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግንባታና ግብአት አቅርቦት ደ/የሥራ ሂደት በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ከ7/10/2012 ዓ.ም እስከ 29/10/2012 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 (ስልሳ) ቀናት እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ80 (ሰማኒያ) ቀናት ድረስ ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት:: እንዲሁም በውል ዘመኑ የፀና መሆን አለበት።
- ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታክስ እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋ ጨምሮ መሆን አለበት::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኤጀንሲው ግንባታና ግብአት አቅርቦት ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ 29/10/ 2012 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት ይከፈታል ፤
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ኤጀንሲው ግንባታና ግብአት አቅርቦት ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ድረስ በአካል በመጎኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058-222-11-00 በመላከ ወይም በስልክ ቁጥር 053222-11-07 በመደወል ማግኘት ይችላሉ ፣
- የጨረታ ሰነዱን በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፖርታል WWW.amhara.gov.et በመግባት የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራከሽን ኤጀንሲ የሚለውን በመክፈት ማየት ይችላሉ፡፡
ፖ. ሣ.ቁ 382 ባህር ዳር
የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ