የተመረተ ማገዶ እንጨት ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ደ/ብርሃን ቅ/ፍ ጽ/ቤት በሰ/ሸዋ ዞን በባሶና ወራና ወረዳ አባሞቴ ቀበሌ ቡራ ደን ላይ የተመረተ የማገዶ እንጨት በሎት 1 የተከፈለ ጠቅላላ ብዛቱ 4196.95 ሜ/ኩ እና በቀይት ቀበሌ ቀርሳ ደን ላይ የተመረተ የማገዶ እንጨት በ 5ሎት የተከፋፈለ ጠቅላላ ብዛቱ 4999.04 ሜ/ኩ እንዲሁም በባሶና ወራና ወረዳ በሳቄሎ ቀበሌ ባቄሎ ተራራ አካባቢ የተመረተ በ3 ሎት የተከፋፈለ ጠቅላላ ብዛቱ 2030.83ሜ/ኩ የተመረተ ማገዶ እንጨት ምርቱ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርቲፊኬት ያላቸውና የዘመኑን የግብር የከፈሉ የሽያጩ መጠን 200.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ የተእታ /VAT/ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ለጨረታ የቀረበውን የደን ምርት ውጤት ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት የደን ምርት ውጤቱ ባለበት ቦታ ተገኝተው ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጨማሪ ዝርዝር መግለጫውን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በማስታወቂያ ሰሌዳ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ /ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ለያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ በመከፈል አማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ደ/ብርሃን ቅርንጫፍ ጽ/ቤትቀበሌ 06 በባሶና ወራና ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ፊት ለፊት በሚገኘው ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- 5 ተጫራቶች ለመግዛት የሚፈልጉት ምርት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) በባንክ ) የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /cpo/ወይም በኢንተርፕራይዙ ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግና የባንክ ደረሰኙን በማያያዝ ወይም እስከ ብር 5,000.00 /አምስት ሺህ/ ድረስ በጽ/ቤት በኩል በማሲያዝ ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተወዳዳሪዎች ለመግዛት የሚፈልጉት ምርት በኦርጅናል ዋጋ መሙያ ቅጽ የሚገዙበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋየ ስምና አድራሻቸውን በመፃፍ በመፈረምና በማተም የጨረታ ፖስታውን በማሸግ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ደ/ብርሃን ቅ/ጽ/ቤት “የማገዶ እንጨት ጨረታ ሽያጭ “ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ጀምሮ 10 የሥራ ቀናት (ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ) እስከ መጨረሻው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ደ/ብርን ቅ/ጽ/ቤት በዚሁ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ተዘግቶ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙበት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ሲሞሉ 15% ተእታን መጨመር የለባቸውም፡፡ ሆኖም አሸናፊው በአሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% ተእታን ጨምሮ ይከፍላል፡፡
- ተጫራቶች ከቀረበው ምርት ከአንድ ሎት በታች መጫረት አይችሉም፡፡
- በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0116375017/0116375030/4 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ
ደ/ብርሃን