ሰርቪስ ኪራይ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2013 ዓ/ም ለቅርንጫፍ ሰራተኞች አገልግሎት የሚውል የሰርቪስ መኪና በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት የምታሟሉ መወዳደር የም ትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ቲን ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና መረጃ ኦርጅናል እና የማይመለስ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ፋይናንስ እናሎጅስቲክ ቢሮ ቁጥር 03 በመሄድ 50 ብር በመክፈል መጥተው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጨረሻ ሰነዶቻቸው ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ 24/03/2013 ዓ/ም ከቀኑ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያውን ከጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ የተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ ቸክ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት መኪኖችን ለማጓጓዝ በሚፈለግበት ወቅት መኪናውን ማቅረብ አለበት፡፡
- ሁሉም የጨረታ ሰነድ ላይ ፊርማ መኖር አለበት፡፡ ስርዝ ድልዝ ካለ በፊርማ ማረጋገጥ አለበት፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 033 551 10 94 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ