የቁም ደን ምርት የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን 3129.41 ሜ/ኩብ ፣ በደቡብ ጎንደር ዞን 22,38369 ሜ/ኩብ እና በደቡብ ወሎ መስተዳደር ዞን 30,429.68 ሜ/ኩብ በተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ የሚገኘውን በድምሩ 55,942,78 ሜ/ኩብ የባህርዛፍ እና የፈ/ጽድ ቁም ደን ምርትን ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች :
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርቲፍኬት ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የሽያጭ መጠን /200,000/ ሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተእታ VAT ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከጨረታው ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለጨረታ የቀረበውን የቁምደን ምርት ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት በቦታው ተገኝተው ማየት ይችላሉ፡፡
- የተጨማሪ ዝርዝር መግለጫዎችን ከጨረታ ሰነዱ ማየት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ውስጥ ቅዳሜን ጨምሮ/ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ በመክፈል አማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ባሕርዳር ቀበሌ 14 አረጋውያን ሕንፃ ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 7 እንዲሁም ምርቱ ካለባቸው ኮምቦልቻ እንጅባራ እና ደ/ታቦር ቅ/ጽ/ቤቶች መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን የቁም ደን ምርት ለመግዛት የሞሉትን ጠቅላላ/ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ባ/ዳር ከተማ ቅ/ርንጫፍ ባንክ ካላቸው ማናቸውም ባንኮች በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ /CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን ቁም ደን ምርት በኦርጅናል ዋጋ መሙያ ቅጽ የሚገዙበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ስምና አድራሻቸው በመፃፍ ተፈርሞ ማህተም በማድረግ የጨረታ ፖስታውን በማሸግ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ባህር ዳር እና ኮምቦልቻ ቅ/ጽ/ቤት የቁም ደን ጨረታ ሽያጭ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 የሥራ ቀናት (ቅዳሜ ጨምሮ) እስከ መጨረሻው 15ኛዉ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል፡፡ የመጨረሻው ቀን የሕዝብ በዓላት ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው ቀን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ 15% ተእታን አይጨምርም፡፡ ሆኖም አሸናፊው በአሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% ተእታን ጨምሮ ይከፍላል፡፡
- ተጫራቾች ከቀረበ አንድ ክፍልፋይ በታች ምርት በታች መጫረት አይችሉም፡፡
- መንገድ የሌለባቸውን ቦታዎች ምርቱን ለማምረትና ለማውጣት የመንገድ ሥራ ኢንተርፕራይዙን በማማከር በአሸናፊው ተጫራች የሚሠራ ይሆናል፡፡
- በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡ለተጨማሪ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር ፡– ዐ582263095/0588719 004/ 0335510118/0116375030/ ደ/ታቦር 0584410306/058 141 09 19 ደውሎ መጠየቅ ይችላል፡፡
- ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የአማራ ደን ኢንተርፕራይ
ባህርዳር