Other Metals / Steel Raw Materials and Products / Water Engineering Machinery and Equipment / Water Pipes and Fittings

የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ለሚገነባው ለጉማራ መስኖ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል Steel Pipe Length 653m, 6mm Thick,800mm Diameter ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በአገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

ሀገር አቀፍ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር NCB AWWCE 05/2013

የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ለሚገነባው ለጉማራ መስኖ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል Steel pipe Length 653m, 6mm thick,800mm diameter ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች የሚከተሉትን ህጋዊ ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡

 1. የዘመኑን ግብር ከፍለው በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የቫት ምዝገባ የምስ ወረቀት እና የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች እነዚህንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ኮፒ በማድረግ በጀርባው ፊርማና ማህተም በማድረግ በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል፡፡
 2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን 90 ቀን እና ከዚያ በላይ ፀንቶ የሚቆይ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) የያዘ በድርጅታችን ስም የተሰራ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና በማሰራት ማስያዝ አለባቸው፡፡ አሸናፊ ከተለየ በኋላ በአሸናፊነት ላልተመረጡ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ከአሸናፊው ጋር ውል ከተያዘ በኋላ የሚመለስ ይሆናል፡፡
 3. ተጫራቾች በዋጋ መሙያ ሰንጠረዡ ለተገለፁት ዕቃዎች የሚያቀርቡት ማስረጃዎችና የሚሞሉትን ዋጋ ኦርጅናል እና ኮፒ ቴክኒካል ስፔስፊኬሽን በተናጠል ከሚያሳይ ብሮሸር ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
 4. ተጫራቾች ዕቃዎቹን የሚያቀርቡበት ጊዜ /Delivery time/ ውል ከተያዘበት ቀን ጀምሮ 90 ቀናት (ዘጠና ቀናት) ይሆናል፡፡
 5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ማለትም የቴክኒከና የዋጋ ሰነዳቸውን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ኮፒና ኦርጅናል ብሎ በመለየት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ባሕር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና /ቤታችን አማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት(አው.ስ.ኮ.ድ) ቢሮ ቁጥር 33 በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡
 6. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 20 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ከቆየ በኋላ 21ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 830 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ቢሮ ህንፃ ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 33 ይከፈታል፡፡ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ መክፈቻ ስነስርዓቱ ላይ ባይገኙም ጨረታው በግዥ ኮሚቴ አማካኝነት ስለሚከፈት ተጫራቾች ከውድድሩ አይታገዱም ነገር ግን በጨረታ መክፈቻ ስነስርዓቱ ለሚወሰዱ ማንኛውም ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ፡፡የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የህዝብ በዓል ከሆነ ወይም የድርጅቱ የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
 7. የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ 7/ሰባት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ተገቢውን የውል ማስከበሪያ የተጫረተበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በድርጅታችን ስም ሲፒኦ ወይም አንኮንድሽናል ባንክ ቢድ ጋራንቲ በማሰራት ማስያዝ እና በአካል ቀርቦ ከድርጅታችን ጋር የውል ስምምነት መያዝ አለበት፡፡ ካልሆነ ድርጅቱ የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው፡፡ የደረሰው ጉዳት ከውል ማስረከቢያው በላይ ከሆነ ድርጅቱ ልዩነቱን በህግ ከአቅራቢው መጠየቅ ይችላል፡፡
 8. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20(ሃያ) ተከታታይ ቀናት በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ቢሮአችን 3 ፎቅ ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ:: የሚገዙ ዝርዝር Psteel pipe Length 653m,6mm thick,800mm diameter አይነትና ብዛት በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
 9. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ይሰረዛሉ፣ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም ይወረሳል ፣ለወደፊቱም ድርጅታችን በሚያወጣው የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል፡፡
 10. የጨረታ ዋጋው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ 60 /ስልሳ/ ቀናት ጸንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡ከተጠቀሰው ቀናት በታች የሰጠ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይደረጋል፡፡
 11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ይህንንም በሚያደርግበት ጊዜ በድርጅቱ የማስታወቂያ መለጠፊያ ቦርድ እና በአካባቢ ማስታወቂያ ይገለፃል፡፡
 12.  ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉበትን ዕቃ ናሙና እንዲያቀርቡ በተጠየቁ ጊዜ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር 058 222 14 79 መደወል ይችላሉ::

አድራሻ ህር ዳር


n