አገር አቀፍ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር NCB AWWCE 02/2013
የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ለሚገነባቸው ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውል K9 DCI PPE DN250mm ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በአገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች የሚከተሉትን ህጋዊ ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
- የዘመኑን ግብር ከፍለው በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የንግድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለበት። ተጫራቾች እነዚህንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ኮፒ በማድረግ በጀርባው ፊርማና ማህተም በማድረግ በመጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን ለ90 ቀን እና ከዚያ በላይ ፀንቶ የሚቆይ 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) የያዘ በድርጅታችን ስም የተሰራ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና በማሰራት ማስያዝ አለባቸው። አሸናፊ ከተለየ በኋላ በአሸናፊነት ላልተመረጡ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ከአሽናፊ ጋር ውል ከተያዘ በኋላ የሚመለስ ይሆናል።
- ተጫራቾች በዋጋ መሙያ ሰንጠረዡ ለተገለፁት ዕቃዎች የሚያቀርቡት ማስረጃዎችና የሚሞሉትን ዋጋ ኦርጅናል እና ኮፒ ቴክኒካል ስፔስፊኬሽን በተናጠል ከሚያሳይ ብሮሸር ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ዕቃዎቹን የሚያቀርቡበት ጊዜ Delivery time/ ውል ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በ 90 ቀናት (ዘጠና ቀናት) ይሆናል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ማለትም የቴክኒክና የዋጋ ሰነዳቸውን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ኮፒ ኦርጅናል ብሎ በመለየት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ባሕር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን አማራ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት (ኢ.ው.ስ.ኮ.ድ) ቢሮ ቁጥር 33 በመቅረብ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ከቆየ በኋላ በ21ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ቢሮ ህንፃ ሶስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 33 ይከፈታል።ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸቸው በጨረታ መክፈቻ ስነ–ስርዓቱ ላይ ባይገኙም ጨረታው በግዥ ኮሚቴ አማካኝነት ስለሚከፈት ተጫራቾች ከውድድሩ አይታገዱም ነገር ግን በጨረታ መክፈቻ ስነስርዓቱ ለሚወሰዱ ማንኛውም ውሳኔዎች ተገዥ ይሆናሉ።የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የህዝብ በዓል ከሆነ ወይም የድርጅቱ የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ7 /ሰባት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ተገቢውን የውል ማስከበሪያ የተጫረተበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በድርጅታችን ስም ሲፒኦ ወይም አንኮንድሽናል ባንክ ቢድ ጋራንቲ በማሰራት ማስያዝ እና በአካል ቀርቦ ከድርጅታችን ጋር የውል ስምምነት መያዝ አለበት ካልሆነ ድርጅቱ የጨረታ ማስከበሪያውን የመውረስ መብት አለው።የደረሰው ጉዳት ከውል ማስረከቢያው በላይ ከሆነ ድርጅቱ ልዩነቱን በህግ ከአቅራቢው መጠየቅ ይችላል።
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20 (ሃያ) ተከታታይ ቀናት በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ14 ከአዲናስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ቢሮአችን 3ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ። የሚገዙ ዝርዝር የK9 DCI PPE DN250mm አይነትና ብዛት በጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
- ጨረታውን ለማባዛት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ይሰረዛሉ፣ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም ይወረሳል፣ለወደፊቱም ድርጅታችን በሚያወጣው የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ ይደረጋል።
- የጨረታ ዋጋው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ቢያንስ ለ60 /ስልሳ ቀናት ጸንቶ መቆየት ይኖርበታል። ከተጠቀሰው ቀናት በታች የሰጠ ተጫራች ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በመሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ይህንንም በሚያደርግበት ጊዜ በድርጅቱ የማስታወቂያ መለጠፊያ ቦርድ እና በአካባቢ ማስታወቂያ ይገለፃል።
- ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉበትን ዕቃ ናሙና እንዲያቀርቡ በተጠየቁ ጊዜ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
ለበለጠ መረጃ ዘወትር በስራ ሰዓት በስልክ ቁጥር– 058 222 14 79 መደወል ይችላሉ::
አድራሻ ባህር ዳር ከተማ