ግልጽ ብሔራዊ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EEU-AEU/NCB/012/2013
የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሥራ አልባሳት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ተቁ |
የአልባሳት ዓይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
1 |
ብሉ ብላክ ፖሊስተር ቪስከስ (GSM መጠኑ 225g)
|
ሜትር |
65,338 |
2 |
ብሉ ብላክ ፖሊስተር ቪስከስ (GSM መጠኑ 200g)
|
ሜትር |
7,312 |
በዚህ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸው ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና፣ በገንዘብ ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው ፣
- የጨረታ ሰነዱን ከታኅሣሥ 6 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 2000.00 (ሁለት ሺህ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸው::
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ኮፒና ኦርጅናል በማለት እስከ ተጠቀሰው የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ በአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት ቀበሌ 16 ኖክ ነዳጅ ማደያ ወይም ኒያላ ሞተርስ ፊት ለፊት ሀቂቃ የገበያ ማዕከል 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ.015 ድረስ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- ጨረታው ታኅሣሥ 27 ቀን 2013 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- ሪጅኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር
0582207469/0583201957 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት