የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ክልል አገልግሎት ለዲስትሪቢዩሽን መስመር ዝርጋታ የሚውል ጥሬ እና የተቀቀለ የእንጨት ምሰሶዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ዝርዝሩም እንደሚከተለው ነው
ሎት |
የዕቃው ዓይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
1 |
የተቀቀለ የእንጨት ምስሶ (9-11) ሜትር |
‘’ |
14,000 |
2 |
ጥሬ የእንጨት ምሰሶ (9-12) ሜትር |
‘’ |
5,500 |
በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡–
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የታደሰ ንግድ ስራ ፈቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፣ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በመንግስት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል በዕቃ እና አገልግሎት አቅርቦት ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው የሚያስረዳ የገንዘብ ሚኒስቴር የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሎት-1 ብር 4000.00 (አራት ሺህ ብር) ለሎት-2 ብር 2000.00 (ሁለት ሺህ ብር) በመከፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- አድራሻ: ባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 16 ኖክ ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት በሚገኘው የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ግዥና ፋሲሊቲ ቢሮ ቁጥር 09።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ለሎት1 ብር 350,000.00 (ሶስት መቶ ሃምሳ ስድስት ሺህ) ለሎት -2 ብር 120,000.00 (አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር) በታወቀ ባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ መሆን ይኖርበታል ።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ በኣንድ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር EEU-AEL/NCB/o07/2012 ሎት1– ወይም EEU-AEU/NCB/007/2012 ሎት-2 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ህዳር 07 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 09 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ፡፡
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቻ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058-220-7469/058-320-1957 መደወል ይችላሉ፡፡
የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት