ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ክልል ህዝቦች ሰማዕታት መታሰቢያ ሀውልት ጽ/ቤት
- የጽህፈት መሣሪያዎች ሎት01፤
- የጽዳት ዕቃዎች ሎት 02፤
- የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ሎት 03፤
- የውሀ ዕቃዎች ሎት 04፤
- ጸረ-አረም፤ጸረ-ተባይ እና ችግኞች እና መሳርያዎች ሎት 05፤
- የደንብ ልብስ 06፤
- የተሸከርካሪ መለዋወጫ 07፤
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃወች 08፤
- የግንባታ ዕቃዎች 09፤
- ፈርኒቸር 10፤ እና
- የህትመት ዕቃወች 11 በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች
የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይገልጻል፡፡
- በመስኩና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ከመንግስት ግዥ ያልታገደ መሆን አለበት፡፡
- የግዥ መጠን ብር 200 ሺህ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሞሉት የመወዳደሪያ ዋጋ መጠን 2 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን በሲፒኦ(በባንክ ደረሰኝ) ወይም በመሂ-1 ለአማራ ክልል ህዝቦች ሰማዕታት መታሰቢያ ሀውልት ጽ/ቤት ስም በማሰራት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊከሌሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በበኩር ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ከ07/03/2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 21/03/2013 ዓ.ም ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 02 ማግኘት ይችላሉ፡
- እያንዳንዱ ዋጋ የሚሞላው በነፃ ገበያ መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሞሉትን የጨረታ ሰነድ በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የአማራ ክልል ህዝቦች ሰማዕታት መታሰቢያ ሀውልት ጽ/ቤት ስም አድራሻ በመፃፍ በማህተምና ፊርማ አስደግፎ ለግዥው ፈፃሚ መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ሰነዱን መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን በ22/03/2013 ዓ/ም በ3፡30 ሰዓት ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት መገኘት በፈለጉ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት አያስተጓጉልም፡፡
- አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በመክፈል ውል ይዞ ያሸነፉበትን ዕቃ (አገልግሎት) ጥራቱን በጠበቀ መልኩ አማራ ክልል ህዝቦች ሰማዕታት መታሰቢያ ሀውልት ጽ/ቤት ድረስ ማድረስ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በጥቅል ወይም በተናጠል ዝቅተኛ ዋጋ የሞላ ይሆናል፡፡
- -የጫራታ ሰነዱን 30ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- -ተጫራቾች የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ የአማራ ክልል ህዝቦች ሰማዕታት መታሰቢያ ሀውልት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582180460 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ክልል ህዝቦች ሰማዕታት መታሰቢያ ሀውልት
ጽ/ቤት