ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ለ2013 በጀት ዓመት አመታዊ
- 1ኛ የፎቶ ኮፒ ማንሣት
- 2ኛ የቢሮ መገልገያ ኤሌክትሮኒክስ እና ማሽኖች ጥገና
- 3ኛ የቢሮና የግቢ ጽዳት እና
- 4ኛ የጋዜጣና መጽሄት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አመታዊ ውል በመያዝ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸው፣
- የግዥው መጠን ከብር 200 ሺህ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ቫት/ ከፋይነት የተመዘገበ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ በፖስታ ማቅረብ አለባቸው ነገር ግን ከላይ ከ1-4 የተጠቀሱትን ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30 በመክፈል በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደ/የስራ ሂደት ክፍል ቢሮ ቁጥር 56 ማግኘት ይቻላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ በቢሮው ቢሮ ቁጥር 50 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ከመክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለፎቶ ኮፒ ማንሣት 3000.00 ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ 1 በመቶ እና ለቢሮ መገልገያ ኤሌክትሮኒክስ እና ማሽኖች ጥገና 1000.00 በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸው በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከሐምሌ 27 ቀን 2012 ዓ/ም እስከ ነሐሴ 11/2012 ዓ/ም ድረስ ለተከታታይ 15 ቀን በአየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ነሐሴ 12/2012 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጐ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 50 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 50 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 2263282 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት