የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የገጠር መንገዶች ኮንስትራከሽን ኤጀንሲ; ነዳጅ፤ ዘይትና ቅባት መግዛት ይፈልጋል

Bid Closing Date: Sep 2, 2019 02:00 PM

ቁጥር አገመኮኤ-02/2012 

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የገጠር መንገዶች ኮንስትራከሽን ኤጀንሲ ለዋናው መ/ቤት፤ ለጥገና ጽ/ቤቶች እና ለፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውል ነዳጅ፤ ዘይትና ቅባት በዘርፉ ከተሰማሩ ሕጋዊ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡

 1. የዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው
 2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው
 3. 50,000,00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
 4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ፤ የተጫራቾች መመሪያ፣ የውል ረቂቅ፤ የዋጋ መሙያ ፎርምና ቴከኒክ መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ አማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ ዋናው ቢሮ ባህርዳር ከተማ ከሚገኘው ከገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 12 የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
 6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የጠቅላላ ዋጋውን 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በማያያዝ በታሸገ ፖስታ አድርገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
 7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሂሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ከኤጀንሲው መ/ቤቱ ግዥ ኦፊሰር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ ነሐሴ 27 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርበታል፡፡
 8. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ እና የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ እስከ 60 (ስልሳ) ቀናት ድረስ ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም በወል ዘመኑ የፀና መሆን አለበት፡፡
 9. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታክስ እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋ ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
 10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከኤጀንሲው ዋናው መ/ቤት ከግዥ ኦፊሰሮች ቢሮ ነሐሴ 27 ቀን 2011 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
 11. የጨረታ ሰነዱን እና የጨረታ ውጤቱን በአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ፖርታል www amhara.gov.et በመግባት የአማራ ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የሚለውን በመክፈት ማየት ይቻላል፡፡
 12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
 13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ከኤጀንሲው ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር፡ . 0582221107 በመደወል ወይም በፋክስ ቁጥር 0582221100 በመላክ ማግኘት ይቻላል፡፡

 

ፖሣ.ቁ.382

ባህር ዳር

አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት

ገጠር መንገዶች ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ