ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2013
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ለ 2013 በጀት ዓመት የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎችን
ማለትም፡-
- ሎት 1. ልዩ ልዩ የአይሲቲ ዕቃዎችን
- ሎት2. ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- ሎት3. ልዩ ልዩ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ ዘዴ ተጫራቾችን አወዳድሮ አሸናፊውን በመለየት ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቾች:-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ሰርተፍኬት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በተጨማሪም ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ 200,000/ሁለት መቶ ሺህ/ ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጨረታው በግልጽ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15/አስራ አምስት ቀን ከቀኑ ከ፡30 ሰዓት ድረስ 50/ሃምሳ/ብር ሰነዱን ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ድረስ በመምጣት መግዛት ይቻላል፡፡ የቴክኒክ እና የፋይናስ ሰነዶችን ለየብቻ በመሙላት በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡ በቴክኒከ ምዘና ያለፉ ተወዳዳሪዎች ወደ ፋይናንስ ውድድር የሚቀርቡ ይሆናል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተመሰከረለት ቼክ/ሲፒኦ/፣ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ቢሮው ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- የሚፈለጉት የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች ዓይነት፣ ብዛትና ስፔስፍኬሽን እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደው አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለው ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ድረስ በመምጣት መውሰድ ይቻላል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 በፋክስ 058 320 70 69 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
አብክመ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት
ባህር ዳር