< Back
የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት የMC-3000 ቢትመን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
የጨረታ ቁጥር አመሥድ 03/2012
ክፍል አንድ
አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት
የMC-3000 ቢትመን ሽያጭ ግልጽ ጨረታ
ድርጅታችን ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተገለፀውን የMC-3000 ቢትመን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ተወዳዳሪ ድርጅት ወይም ግለሰብ በድርጅታችን ዋናው መ/ቤት ድረስ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላል፡፡
ተ.ቁ |
የዕቃው አይነት |
መለያ |
መለኪያ |
ብዛት |
የሚገኝበት ቦታ |
1 |
MC-3000 ቢትመን
|
|
ቁጥር
|
4,500 |
ፍቼ ፕሮጀክት
|
ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለፁትን የጨረታ መወዳደሪያ መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም ድርጅት ወይም ግለሰብ በጨረታው መወዳደር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች በድርጅታችን ስም ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል የጠቅላላ ዋጋውን 10% ሲ.ፒ. ኦ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል ባንክ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ አሽናፊውን ተጫራች ድርጅት ወይም ግለሰብ በሚመርጥበት ጊዜ የሚሸጠውን ቢትመን መጠን እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 50% ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዥ ለተገለፁት እቃዎች የሚያቀርቡበትን መግዣ ዋጋ በፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሰውን ቢትመን በድርጅታችን ፍቼ አስፓልት መንገድ ስራ ፕሮጀክት በአካል መጥቶ ማየት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች መወዳደሪያ ሰነዳቸውን ማለትም ፋይናንሽያል ሰነድ አዘጋጅተው እስከ 20ኛው ቀን ድረስ ባህርዳር ከተማ በሚገኘው ዋና መ/ቤታችን አማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ፊት ለፊት የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ20ኛው ቀን ከቀኑ 9:00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 9:30 ይከፈታል፡፡
- በጨረታው ለተገለፁት እቃዎች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ብር 100.00 (መቶ ብር ብቻ በመክፈል ከድርጅታችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 23 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው አሸናፊ ድርጅት ማሸነፉ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀን ውስጥ ውል መውሰድ አለበት፡፡ በዚህ ቀን ውስጥ ውል ካልወሰደ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ይወረሳል፡፡
- በተጨማሪም አሸናፊው ድርጅት ውል ከወሰደ በኋላ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እቃዎችን ሙሉ በሙሉ ማንሳት አለበት፡፡ በተባለው ቀን ካላነሳ መ/ቤቱ ለሌላ ድርጅት የመሸጥ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን አሽናፊው ድርጅት እቃዎችን መርጦ መውሰድ ወይም መተው አይችልም፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 35-76 መደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት