የአግሮስቶን ቴክኖሎጂ የአዋጭነት ጥገናት ሰነድ ዝግጅት የአገልግሎት ግዥ የግልጽ ጨረታ፣ ማስታወቂያ
የጨረታ ሰነድ ቁጥር 40/2013
የአማራ ሕንጻ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ለባህርዳር ግንባታ ግብኣት ማምረቻ ማእከል እና ለደሴ የግብአት ማምረቻ ተቋማ ገራዶ ለሚገኘው የአግሮስቶን ማምረቻ ግብአቶችን ከውጭር እያመጣ የሚጠቀምባቸው ፋይበር ግላስ እና ማግኒዥየም ክሎራይድ ከኦሮሚያ ክልል ማግኒዥየም ኦክሳይድ እና ፑሚስ ግብአቶችን እያሰመጣ የተለያዩ የአግሮስቶን ምርቶችን በሰው ሃይል ሲያመርት መቆየቱ ይታወቃል ። ስለሆነም ቴከኖሎጂውን ተወዳዳሪ እና ውጤታማ ለማድረግ በተጨማሪም ቴከኖሎጂው በቀጣይ ያለው አዋጭነት ፤ ስለ ግብዓቾችና ስለገበያ ተፈላጊነቱ በማጥናት ሰነድ ለማዘጋጀት በቀጣይ ድርጅቱ ስለቴክኖሎጂው መሻሻል ወይም ሌላ አማራጮችን ለመወሰን የሚረዳ የአግሮስቶን ቴክኖሎጂው የአዋጭነት ጥናት ማስጠናት ስለሚፈልግ ህጋዊ ከሆኑ ፈቃድ ካላቸው የአገልግሎቱ አቅራቢዎች መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድር ማስጠናት ይፈልጋል ስለዚህም፡በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ በአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅ ቀበሌ 11 ኮብል አክሲዮን ማህበር ፊትለፊት ወደ ዲያስፖራ በሚወስደው መንገድ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮለ15 ተከታታይ ቀናት በብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/በመክፈል መወሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የአንዱን ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋውን በጨረታ መምሪያው መሰረት በመሙላት“የቴከኒከ ማወዳደሪያ ሰነድ ፤ የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ” እና “የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ ማስያዣና በ 2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያው ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴከኒካል መወዳደሪያው ሰነድ ካለበት ፖስታ ውስጥ አስገብቶ በማሸግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር) ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ብቻ ባህርዳር በተዘጋጀው የድርጅቱ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆን ሰሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከላይ በተገለጸው መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሸኝ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከቀኑ 8፡30 ሠዓት ባህር ዳር ከተማ አባይ ማዶ ቀበሌ 11 ዲያስፖራ በሚወስደው አስፓልት መስመር 500ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው የደርጅቱ፡ ቢሮ ቁጥር 18 የቴክኒካል ሰነድ ብቻ ተጫራቾች ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ ይከፈታል፤ በቴክኒካል ውጤት 70% እና በላይ ያገኙ ተጫራቶች ብቻ ለዋጋ ውድድር እንዲገኙ ጥሪ ይደረግላቸዋል በቴክኒክ መስፈርቱ ከ70% በታች ያገኙ ተወዳዳሪዎች እሸናፊ አለመሆናቸው ተገልጾላቸው የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ ሳይከፈት ይመለስላቸዋል፡፡
- በሚቀርበው የጨረታ ሰነድ መሟላት ያለበት
- በዘርፉ የንግድ ስራ ፈቃድና ለዘመኑ ስለመታደሱ ማረጋገጫ
- የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ
- ማንኛውም የወቅቱን የመንግስት ገቢ ግብር ለመክፈላችሁ ወይም ሌሎች ግዴታዎችን ስለመወጣታቸው ማረጋገጫ ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/TIN/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት /VAT/Reg. Certificate
- የአዋጭነት ጥናት ማካሄዱን የመልካም ስራ አፈጻጸም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
4 የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል። ነገር ግን የሚያሲዘው ማስከበሪያ ከብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) መብለጥ የለበትም፡፡
5 የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀንጀምሮ ለ45 ተከታታይ ቀናት ፀንቶይቆያል።
6 የጨረታ ተወዳዳሪዎች በሌሎች ተወዳዳሪዎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የቴክኒክ ማወዳደሪያ ሰነድ” እና “የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ እንዲሁም ጨረታ ማስከበሪያውን ጨምሮ በተለያዩ ኢንቨሎፖች ለየብቻ በጥንቃቄ አሽገው በእንድፖስታ በማጠቃለል እና በማሸግ በጨረታ ሰነዱ በእያንዳንዱ ገጽ እና ፖስታው ላይ ስምና ፊርማቸውን፤ ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ሊኖር ይገባል፡፡
8. ሻጭ የቴከኖሎጂውን የአዋጭነት–ጥናት ሰነድ በማዘጋጀት አስረክቦ ሲጨርስ የሚጠይቀውን ከፍያ በባንክ እንዲላከለት ከፈለገ የባንክ መላኪያው ከሚላከው ገንዘብ ላይ ይቀነሳል፡፡
9. ከጨረታ ሳጥን መዝጊያ ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ ተጫራች ተቀባይነትአይኖረውም፡፡
10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡ በመሆኑም ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ ድርጅቱ ሀላፊነት አይወስድም
11. ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ በአካል በመገኘት ወይም ከዚህ በታች በተጠቀሱት አድራሻዎች ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
ስልክ ቁጥር፡-058-218-09-58
ፋክስ ቀጥር፡-058-218-07-11/058-218-05-42
የአማራ ሕንፃ ሥራዎች
ኮንስትራክሽን