Accounting and Auditing / Accounting System Design

የአማራ ሕንጻ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ከጥቅምት 01/2011 ዓ/ም እስከ ጥር 30/2012 ዓ/ም ድረስ ያለውን የቫት ደረሰኝ በዝርዝር ምዝገባ ተደርጎ ምርመራ/ኦዲት ማድረግ/ የአገልግሎት ግዥ ህጋዊ ከሆኑ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

የቫት ደረሰኝ ምርመራ በዝርዝር ምዝገባ ኦዲት ማድረግ

የአገልግሎት ግዥ ግልጽ ጨረታ በድጋሚ የወጣ ማስታወቂያ

 የአማራ ሕንጻ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ከጥቅምት 01/2011 / እስከ ጥር 30/2012 / ድረስ ያለውን የቫት ደረሰኝ በዝርዝር ምዝገባ ተደርጎ ምርመራ/ኦዲት ማድረግ/ የአገልግሎት ግዥ ህጋዊ ከሆኑ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በበኩር ጋዜጣ ጨረታ አውጥተን የነበረ ቢሆንም በኮረና ቫይረስ ምክንያት ቢሮ ተዘግቶ ስለነበረ የጨረታ ሰነዱ ሳይሸጥ ቀርቷል፡፡ ስለዚህ በድጋሚ በወጣው ጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ የጨረታ ሰነዱን /ዳር ከተማ በአማራ ሕንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቀበሌ 11 ወደ ዲያስቦራ በሚወስደው አስፓልት 500 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 11 የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ::

 1. ተጫራቾች ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር) ከቀኑ 8:00 ሠዓት ድረስ ብቻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8:00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 2. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከቀኑ 830 ሠዓት ባህርዳር በሚገኘው በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 18 ይከፈታል፡፡
 3. በሚቀርበው የጨረታ ሰነድ መሟላት ያለበት፡፡

  • 3.1 በዘርፉ የንግድ ስራ ፈቃድና ለዘመኑ ስለመታደሱ ማረጋገጫ እና የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ
  • 3.2 ማንኛውም የወቅቱን የመንግስት ገቢ ግብር ለመክፈላችሁ ወይም ሌሎች ግዴታዎችን ለመወጣት ማረጋገጫ፣
  • 3.3. የግብር ከፋይነት መለያቁጥር/TIN/እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት VAT Reg. Certificate/
  • 3.4. የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፣ ነገር ግን የሚያዘው ማስከበሪያ ከብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) መብለጥ የለበትም፡፡
 4. የጨረታ አሸናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ከሶስት የስራ ቀናት በኋላ ባሉት አምስት የስራ ቀናት ውስጥ ለአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10% የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና ፐርፎርማንስ ቦንድ/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያስይዛል፡፡ከላይ በተገለጸው ቀን ውል ያልፈጸመ እንደሆነ ግዥ ፈፃሚው አካል የጨረታ ማስከበሪያ የመውረስ መብት ይኖረዋል፡፡
 5. አሸናፊ ከተለየ በኋላ በሸናፊነት ያልተመረጡ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ከአሸናፊው ጋር ውል ከተያዘ በኋላ ይመለስላቸዋል፡፡
 6. ድርጅቱ ከአሸናፊው ድርጅት የስራውን ትክክለኛነት እና የጥራት ደረጃ በድርጅቱ ባለሙያዎች በማረጋገጥ ትክክለኛነቱን ሲያሟላ ብቻ ሊረከብ ይችላል፡፡
 7. በጨረታው ቅር የተሰኘ ተጫራች የጨረታ ውጤቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ 3 የስራ ቀናት ብቻ ቅሬታው ማቅረብ ይችላል፡
 8. የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ 45 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆያል፡፡
 9. የጨረታ ተወዳዳሪዎች በሌሎች ተወዳዳሪዎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
 10. በጨረታ ሠነዱ በእያንዳንዱ ገጽ እና ፖስታው ላይ የድርጅቱ ፊርማና ማህተም ሊኖር ይገባል፡፡
 11. ድርጅቱ የጨረታ አሸናፊ ከሆነው አቅራቢ የጨረታውን ይዘት ሳይቀይር ከግዥ አገልግሎቱ ጠቅላላ መጠን ላይ 50% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፡፡
 12. ሻጭ ስራውን አስረክቦ ሲጨርስ የሚጠይቀውን ክፍያ በባንክ እንዲላክለት ከፈለገ የባንክ መላኪያው ከሚላከው ገንዘብ ላይ ይቀነሳል፡፡
 13. ከጨረታ ሳጥን መዝጊያ ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
 14. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡ በመሆኑም ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ ድርጅቱ ሀላፊነት አይወስድም
 15. ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ በኣካል ቢሮ ቁጥር 18 በመገኘት ወይም ከዚህ በታች በተጠቀሱት አድራሻዎች ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ስልክ ቁጥር 058218-09-58

ፋክስ ቁጥር፡-058-218-07-11/542

የአማራ ሕንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት

ባህርዳር