Building and Finishing Materials / Building Construction / Sanitary and Ceramics

የአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ውል ይዞ እየገነባ ለሚገኘው ለወልዲያ ከተማ አስ/ቢሮ ግንባታ ፣ ለለጋምቦ ቢሮ ግንባታ እና ወረባቦ ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክቶች ግንባታ አገልግሎት የሚውል የግንባታ ማጠናቀቂያ እቃዎች የአቅርቦት እና አቅርቦትና ገጠማ ስራ አቅርቦት (ፒቪሲ ታይል፤ ፒቪሲ ሰከርቲንግ፤ የወለል ሴራሚከ፤ የግድግዳ ሴራሚክ፤ ሴራሚክ ስከርቲንግ እና ቴራዞ ዊንዶ ሲል) እንዲሁም የአቅርቦትና ገጠማ ስራ (ግራናይት ፔንት) ለመግዛት ህጋዊ እና ፍቃድ ያላቸውን አቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 10/2013

 1. የአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ውል ይዞ እየገነባ ለሚገኘው ለወልዲያ ከተማ አስ/ቢሮ ግንባታ፣ ለለጋምቦ ቢሮ ግንባታ እና ወረባቦ ቢሮ ግንባታ ፕሮጀክቶች ግንባታ አገልግሎት የሚውል የግንባታ ማጠናቀቂያ ዕቃዎች የአቅርቦት እና አቅርቦትና ገጠማ ስራ አቅርቦት (ፒቪሲ ታይል፤ ፒቪሲ ሰከርቲንግ፤ የወለል ሴራሚከ፤ የግድግዳ ሴራሚክ፤ ሴራሚክ ስከርቲንግ እና ቴራዞ ዊንዶ ሲል) እንዲሁም የአቅርቦትና ገጠማ ስራ (ግራናይት ፔንት) ለመግዛት ህጋዊ እና ፍቃድ ያላቸውን አቅራቢ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው ድርጅቶች፣ የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ በሚገኘው የአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቀበሌ 11 ወደ ዲያስፖራ መንደር በሚወስደው አስፓልት ከዋናው አስፓልት መንገድ 500 ሜ ገባ ብሎ ቢሮ ቁጥር 16 ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በብር 200 መግዛት እና መውሰድ ይችላሉ።የጨረታው ውድድር በሎት /በምድብ ድምር ዋጋ የሚታይ ሲሆን በአንድ ሎት በምድብ/ ለተጠየቁዕቃዎች ለሁሉም (ሙሉ በሙሉ) ዋጋመሙላት እንዳለባችሁ እናሳስባለን። ነገር ግን ለድርጅቱ የተሻለ ጥቅም ያስገኛል ተብሎ ከታመነበት በድርጅቱ መመሪያ ገጽ 14 አንቀጽ 14.2.1 ተራቁጥር 4 መሰረት ውድድሩን በነጠላ ዋጋ በማወዳደር ዝቅተኛ የሆነውን በመምረጥ ግዥ ሊፈጸም ይችላል።
 2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን (16 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር) ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ብቻ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
 3. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከቀኑ 8፡30 ሠዓት በድርጅቱ፡ ቢሮ ቁጥር 18 ይከፈታል። ስሚቀርበው የጨረታ ሰነድ መሟላት ያለበት፡3.1 በዘርፉ የንግድ ስራ ፈቃድና ለዘመኑ ስለመታደሱ ማረጋገጫ፣3.2.ማንኛውም የወቅቱን የመንግስት ግብር ለመከፈሉ ወይም ሌሎች ግዴታዎችንስለመወጣት ማረጋገጫ፣3.3 የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (tiN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣3.4 የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፤ ነገር ግን የሚያስይዘው ማስከበሪያ ከብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) መብለጥ የለበትም።3.5 ድርጅቱ ከአሸናፊው ድርጅት ንብረቱን ከመረከቡ በፊት ናሙና አስቀርቦየዕቃዎችን ትክክለኛነት የጥራት ቴስት በማሰራት እና በድርጅቱ አማካሪዎችበማረጋገጥ ትከክለኛነቱን ሲያሟላ ብቻ ይረከባል። ከህጋዊ ተቋማት ለሚደረግየጥራት ማረጋገጫ ከፍያ በሻጭ ይሸፈናል።3.6 በጨረታው ቅር የተሰኘ ተጫራች የጨረታ ውጤቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ 3የስራ ቀናት ብቻ ቅሬታውን ማቅረብ ይችላል።
 4. በጨረታ ውድድሩ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ዕቃዎችን በራሱ ወጪ ፕሮጀክቶቹ በሚገኙበት ከተማ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ በማቅረብ ያስረከባል።
 5. የጨረታ አሸናፊው ለአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10% የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና /የውል ማስከበሪያ/ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያስይዛል።
 6. የጨረታ ሰነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆያል።
 7. የጨረታ ተወዳዳሪዎች በሌሎች ተወዳዳሪዎች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችሉም።
 8. በጨረታ ሠነዱ በእያንዳንዱ ገጽ እና ፖስታው ላይ የድርጅቱ ፊርማና ማህተም ሊኖር ይገባል።
 9. ድርጅቱ የጨረታ አሸናፊ ከሆነው አቅራቢ የጨረታውን ይዘት ሳይቀይር ከገዛው ዕቃ መጠን ላይ በየሎቱ ጠቅላላ ዕቃ አይነትና መጠን ወይም በእያንዳንዱ የዕቃ አይነትና መጠን ለገዥ ጠቃሚ ነው ብሎ ከታመነ ውል ሲይዝ 50% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
 10. . ከጨረታ ሳጥን መዝጊያ ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም።
 11. አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ውለታ ወስዶ ናሙና ለአማካሪ በማቅረብ ሲፀድቅለት ብቻ ያቀርባል። ገጠማ የተጠየቀባቸውን ዕቃዎች አቅርቦ ይገጥማል።
 12. ውድድሩ በሎት ድምር ኣሸናፊ የሚል ቢሆንም ገዥ ድርጅቱን የሚጠቅም ሆኖ ከተገኘ በነጠላ ዋጋ በማወዳደር አሸናፊ ሊመርጥ ይችላል።
 13. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝመብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 058-218-0711/ 09-18-53-14-16

የአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት