ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የአመድጉያ የበግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት የ2013 በጀት ዓ.ም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- አላቂ የፅ/መሣሪያዎች
- የቢሮ የጽዳት ዕቃዎች፡
- የህንፃ መሣሪያዎች
- የሰራተኞች የደንብ ልብስ (አልባሳት)
እነዚህን ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ የንግድ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
ተወዳዳሪዎች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ መኖር አለበት፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN Number/ ተመዝጋቢና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ጠቅላላ ግዥው ወይም ዋጋው ከ200,000 /ከሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን መ/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ በተናጠል ዋጋም ሆነ በጥቅል ወይም በሎት መ/ቤቱ የሚያወዳድር መሆኑን ማወቅ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ከላይ ከተቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታችውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒውንና ኦርጅናል ሰነዶቻቸውን ማቅረብና ማመሳከር ይኖርባቸዋል፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎች ዓይነትና ዝርዝር ስፔስፊኬሽን መ/ቤታችን በአማርኛ ቋንቋ ያዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 15 (አስራ አምስት) ብር በመከፈል ከቢሮ ቁጥር 5 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ/ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚችል እና በጨረታው ላይ ችግር ቢከሰትና ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ በራሱ ምክንያት ውል ባይፈፅም ያስያዘውን 1% የሚወረስ መሆኑንና አቅርቦቱን ካሸነፈ ለውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ የሚችል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሁለት ኮፒ የሚመለከታቸውን ሰነዶች በሙሉ በማድረግ ስርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በአየር ላይ ቆይቶ በእለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በማግስቱ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማዕከላችን በግ/ፋ/ን/አ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም ጽ/ቤቱ ጨረታውን የሚከፍት ይሆናል፡፡
- መ/ቤታችን ከሚገዛው ዕቃ 20% /ሃያ ፐርሰት/መጨመር ውይም መቀነስ ይችላል፡፡
- ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በተጨማሪ ማስረጃ በስልክ ቁጥር 011-892-2459፣ 011-892-3615 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በአብክመ እ/ሀ/ል/ማ ኤጀንሲ በመንዝ
ጌራ ምድር ወረዳየአመድ ጉያ የበግ
ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል