የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት በስልጤ ዞን የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ፅ/ቤት ለ2013 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚያስፈልጉትን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ለቢሮ መገልገያ የሚሆኑ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የሚፈለጉ የዕቃ ዓይነቶች:
- ሞተር ሳይክል
- ስቴሽነሪ
- የኤሌክትሮኒክስ
- ኢምፖርትድ ፈርኒቸር
- የግንባታ ዕቃዎች
- የጀነሬተር
- የሞተር ስፔር–ፓርት
- የእንስሳት መድኃኒት
- የውሃ ፓምፕ
- ሎካል ፈርኒቸር
- የደንብ ልብስ
- የህትመት ሥራ
- የትምህርት ኬሚካል
- የውሃ ዕቃ
በመሆኑም ተጫራች ድርጅቶች :
- በተሰማሩበት ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ማናቸውም ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ የማይመለስ 70 ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከቢሮ ቁጥር 02 በመውሰድና በመሙላት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን። እንዲሁም ተጫራች ድርጅቶች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ሲፒኦ ለተራ ቁጥር 17,000.00 (አስራ ሰባት ሺህ ብር)፣ ለተራ ቁጥር 2፣3፣4፣5፤6 እና 14 ለእያንዳንዳቸው 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በተራ ቁጥር 7፤8፤9፤10፤11፤ 12 እና 13 ለእያንዳንዳቸው 3,000.00 (ሦስት ሺ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል። በመሆኑም ጨረታው የሚከፈተው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከ21ኛው ቀን በኋላ ባለው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባልተገኙበት/ ከቀኑ በ6፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 09 ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡– መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡– 09 13-34-51-26 ወይም 09-10-03-64-12
የአልቾ ውሪሮ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ፅ/ቤት